“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ
ዲ.ዩ፤ ሚያዝያ 7/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና እንደሚጫወቱ የተገለጸው…
ዲ.ዩ፤ ሚያዝያ 7/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና እንደሚጫወቱ የተገለጸው…
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ከዚህ ቀደም ዲላ ዩኒቨርሲቲ በዶመርሶ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር መንደር ያለማቸውና ምርታማነታቸው በምርምር የተረጋገጠ የእንሰት ዝርያዎችን ለይርጋጨፌ ወረዳ አርሶ አደሮች ማሰራጨቱን መግለጻችን ይታወሳል። በዛሬው እለትም የተሻሻሉ የእንሰት ችግኞች በገደብ ወረዳ ለሚገኙና ችግኞችን የመግዛት አቅም ለሌላቸው አርሶ አደሮች አሰራጭቷል።
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 28/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት እና አጋርነት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በጌዴ ዞን ለሚገኙ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች በመሰረታዊ የቀዶ ህክምና ነርሲንግ አገልግሎት እና ኢንፌክሽን መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ ለሁለት ተከታታይ ቀናት ስልጠና ተሰጥቷል።
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 27/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የመምህራን እና ተመራማሪዎችን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ በምርምር ጽሁፍ ረቂቅ አጻጻፍ፣ በአሳታሚ ምርጫ እና በማሳተም ዙሪያ በሃሴ ዴላ ግቢ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ዲ.ዩ፣ መጋቢት 27/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት አጋርነት ዳይሬክቶሬት የተሻሻሉና ምርታማነታቸው በምርምር የተፈተሸ የእንሰት ዝርያዎችን ስርጭት አካሂዷል።
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 27/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት እና አጋርነት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከጌዴኦ ዞን መምሪያ፣ ከምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ እና ከሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳዎች ለተወጣጡ የሰላምና ፀጥታ ባለሙያዎች በሰላም እሴቶች ግንባታ ላይ ያተኮረ ስልጠና ለተከታታይ ሶስት ቀናት ተሰጥቷል።
ዲ.ዩ፦ መጋቢት 26/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ እና መደ ወላቡ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን የመግባቢያ ሰነድ ነው የተፈራረሙት።
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 26/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ለተማራማሪዎች፣ ለውስጥ ሰራተኞች እና ለባለድርሻ አካላት በቡና ጥራት ቅምሻ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 25/2015 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የሴቶችን የአመራርነትና የውሳኔ ሰጪነት ሚናን ለማጎልበት ለዲላ ከተማ ምክር ቤት ሴት ተመራጮችና አመራሮች የአቅም ግንባታ ሰልጠና ተሰጥቷል።
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 20/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ 4ተኛውን ሳምንት የላብራቶሪ ኤግዚብሽን አካሂዷል።
አንተነህ ወጋሶ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ዲን በወቅቱ እንደገለጹት፤ የላብራቶሪ ኤግዚብሽኑ ላለፉት ሦስት ተከታታይ ሳምንታት እየተካሄደ መቀጠሉን ገልጸው፤ በባለፈው ሳምንት በኮሌጁ በተያዘው ማንዋል መሰረት በኤግዚብሽኑ የኮሌጁ የውሃ ሃብት እና መስኖ ምህንድስና ት/ቤት ላብራቶሪዎቻቸውን ማቅረባቸውን ገልጸዋል።