የሀገር አቀፍ መታወቂያን (National ID) ይመለከታል

በሀገር አቀፍ ደረጃ ክፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶ ለዜጎች ሀገር አቀፍ መታወቂያ (National ID) በመዘጋጀት ላይ መሆኑ ይታወቃል። በዚህም መሰረት ከጠቅላይ ሚኒስቴር ፅ/ቤት ባለሙያዎች ወደ ዩኒቨርሲቲያችን መጥተው ለተማሪዎች ሀገር አቀፍ መታወቂያ የማዘጋጀት ስራ ነገ ቅዳሜ 18/2014 ዓ.ም ከጧት 2:00 ጀምሮ የሚያከናውኑ ይሆናል።
ስለሆነም የዩኒቨርሲቲያችን ተማሪዎች በሙሉ በተጠቀሰው እለትና ሰአት በዋናው ግቢ የምትገኙ በሴኔት መሰብሰቢያ አዳራሽ፣ በኦዲያአ ግቢ የምትገኙ በArchitecture Lab, በሀሴዴላ ግቢ የምትገኙ በመማሪያ ክፍል እና በሪፌራል ሆስፒታል ግቢ የምትገኙ ደግሞ በICT Room ተገኝታችሁ ፎቶ እንድትነሱ እና ቅፅ እንድትሞሉ ዩኒቨርሲቲው በጥብቅ ያሳስባል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

‹‹የሀገሩን ሰርዶ በሀገሩ በሬ››

የሀገረ¬ ሰብ (ሀገር በቀል) እውቀት ማለት ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ የህይወት መስተጋብሮችን የሚቃኙ ፍልስፍናዎች የሚዳሰሱበትና መፍትሄ የሚሰጥበት፣ የተገለፀና ያልተገለፀ እውቀትና ልምድን ያጠቃልላል፡፡ በብዙ ዘመናት ልምድ የዳበረና በባህል ውስጥ ሰርፆ ከትውልድ ትውልድ በታሪክ፣ ዘፈን፣ ዳኝነት፣ ህክምና፣ ጥበብ፣ አባባል፣ እምነት እና በሌሎች መንገዶች በአካባቢው ቋንቋ የሚተላለፍ የጋራ ወይም የወል እውቀት ነው፡፡ እውቀቶቹ በተገኙበት ቦታ ምንጭ ለሆኑት ግለሰብና ቤተሰብ የተሰጠ ልዩ ጥበብ ይሁን እንጅ በጊዜ ሂደት በአካባቢው ማህበረሰብ እየተለመደና እየሰፋ ሲመጣ የጋራ ንብረት ይሆናል፡፡

በሐሴዴላ ግቢ ለተመደቡ አዲስ ገቢ ተማሪዎች በአካባቢውና በዩንቨርሲቲው ማህበረሰብ ደማቅ አቀባበል እየተደረገላቸው ይገኛል

ዲ.ዩ፦ ሰኔ 15/2014 ዓ.ም. (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሀሴዴላ ግቢ አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎችን በመቀበል ላይ ነው።
በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተመደቡ ከሁለት ሺህ ሁለት መቶ በላይ ተማሪዎች ናቸው በግቢው አቀባበል እየተደረገላቸው ያሉት።
አዲስ ገቢ ተማሪዎቹን የዩኒቨርሲቲው፣ የጌዴኦ ዞን አስተዳደር እና የዲላ ከተማ አስተዳደር አመራር አባላት እንዲሁም የሀገር ሽማግሌዎች፣ የፌደራል እና የአካባቢ የፀጥታ አስከባሪዎች፣ የአካባቢው ማሕበረሰብ አባላት አቀባበል እያደረጉላቸው ነው። በተያያዘም የተማሪዎች ህብረት አባላት፣ የአካባቢው ወጣቶች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት በአቀባበሉ ላይ የነቃ ተሳትፎ በማድረግ ተማሪዎቹን እያገዙ መሆኑን ተመልክተናል፡፡

የጌዴኦ ዞን ወጣቶች እና ፀጥታ አካላት ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በመተባበር ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች አቀባበል እያደረጉ ነው

የጌዴኦ ዞን ወጣቶች እና ፀጥታ አካላት ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ጋር በመተባበር ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች አቀባበል እያደረጉ ነው።
ባለ አንፀባራቂ የደንብ ልብስ የለበሱ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችና የጌዴኦ ዞን ወጣት አደረጃጀት አባላት ከፖሊስ አካላት ጋር በመሆን ነው ለተማሪዎቹ አቀባበል እያደረጉ ያሉት። ተማሪዎቹን "እንኳን ወደ ዉቢቷና ለምለሚቷ ዲላ ከተማ ደህና መጣችሁ" እያሉ ዩኒቨርሲቲው በመደበላቸው አውቶብሶች ያለ እንግልት እቃቸውን ጭምር በመጠበቅ በኢትዮጵያዊ ፍቅር እየተቀበሏቸው ይገኛሉ::
ወደ እንግዳ ተቀባይዋ የጌዴኦ ዞን መዲና ዲላ "የእንኳን ደህና መጣችሁ" አቀባበል ነገና ከነገ ወዲያም ይቀጥላል። ተማሪዎቹን ከከተማዋ መግቢያ አቤኔዘር ሆቴል ፊት ለፊት ተቀብሎ ወደ ተመደቡባቸው ግቢዎች የመሸኘቱ ስራ በዋናነት ነገና ከነገ ወዲያም እንደሚቀጥል ለማወቅ ችለናል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ባስገነባው ሀሴዴላ ግቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅት መጠናቀቁን አስታወቀ

ዲ.ዩ፦ ሰኔ 13/2014 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ባስገነባው ሀሴዴላ ግቢ ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር ዝግጅት መጠናቀቁን አስታወቀ። ዩኒቨርሲቲው ሰኔ 15 እና 16፣ 2014 ዓ.ም አዲስ ገቢ የቅድመ ምርቃ መደበኛ ተማሪዎችን እንደሚቀበልም ነው የተገለፀው፡፡
በዩኒቨርሲቲው የአስተዳደርና ተማሪዎች አገልግሎት ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ዳዊት ሀዬሶ ተቋሙ በትንሽ ተማሪዎች እና በአንድ ግቢ አገልግሎት ከመስጠት በጊዜ ሂደት አሁን ያለበት ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል። ዲላ ዩኒቨርሲቲ ዛሬ ላይ ዋናውን ግቢ ጨምሮ፣ ኦዳያአ፣ ሆስፒታል እንዲሁም ዘንድሮ አዲሱን ሀሴዴላ ግቢ በይፋ ስራ አስጀምሮ በአራቱ ግቢዎች በርካታ ተማሪዎችን የማስተናገድ አቅም ገንብቷል ብለዋል ዶ/ር ዳዊት፡፡

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሀሴዴላ ግቢን ስራ ለማስጀመር ያለመ ውይይት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ተካሄደ

ዲ.ዩ፦ ሰኔ 13/2014ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሀሴዴላ ግቢን ስራ ለማስጀመር አላማው ያደረገ ወይይት ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ተካሄደ።
በውይይቱ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ዶ/ር ችሮታው አየለ የሀሴዴላ ግቢ ካሉት ሌሎች ግቢዎች በበለጠ ከፍተኛ በጀት ተመድቦ ሰፋፊ ግንባታዎች የተከናወኑበት ነው ብለዋል። ዶ/ር ችሮታው አክለውም ግቢው በተገነባበት መሬት ላይ ለዘመናት ሲያለሙና ሲኖሩ የነበሩ የአካባቢው ማህበረሰብ አባላት ቦታውን "ለዚህ ትልቅ ልማት እንድናውል በፍቃደኝነት ስለ ሰጡን ከምንም በላይ በእራሴ እና በዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ስም ላመሰግናቸው እወዳለሁ" ብለዋል።

በዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሪፌራል ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል አዲስ የአሰራር ሰርአት ተዋወቀ

ዲ.ዩ፦ ግንቦት 27/2014 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) በዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሪፌራል ሆስፒታል አገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ችግሮችን መፍታት የሚያስችል አዲስ የአሰራር ሰርአት መተዋወቁ ተገለፀ። አዲሱ ችግር ፈቺ የአሰራር ስርአት ከዚህ ቀደም ሲንከባለሉ የመጡ ችግሮችን በዘላቂነት በመፍታት ሆስፒቲሉ የተሻለ እና ጥራቱን የጠበቀ አገልግሎት ለማህበረሰቡ ለመስጠት እንዲችል የሚረዳ ነው ተብሏል።
አዲሱን የአሰራር ስርአት ለማስተዋወቅ በተዘጋጀው መርሃግብር የዲላ ዩኒቨርሲቲ ህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ሪፌራል ሆስፒታል ምክትል ፕሬዝዳንትን ጨምሮ፣ የሆስፒታሉ አመራር አባላት፣ ልዩ ሀኪሞች፣ ዳይሬክተሮች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ የስራ ሂደት አስተባባሪዎች እና የህክምና አገልግሎት ዘርፍ ኃላፊዎች ተሳታፊ ሁነዋል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ እፅዋት ጥበቃና ኢኮቱሪዝም ማዕከል ከጌዴኦ ዞን ለተወጣጡ የባህል መድሃኒት አዋቂዎች ግንዛቤ የሚረዳ ወይይት አዘጋጀ

ዲ.ዩ፦ ግንቦት 29/2014 ዓ ም(ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ እፅዋት ጥበቃና ኢኮቱሪዝም ማዕከል ከጌዴኦ ዞን ለተወጣጡ የባህል መድሃኒት አዋቂዎች ግንዛቤ የሚረዳ ወይይት አዘጋጅቷል። እንደ ሀገር በተቀመጠው የጤና ፖሊሲ መሰረት በሽታን መከላከል ቀዳሚ አቢይ ጉዳይ መሆኑን ያወሱት የዩኒቨርሲቲው ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዶ/ር ደረጀ ክፍሌ ከዚሁ ባለፈ የታመሙትን በማከም ጤናው የተጠበቀ ማህበረሰብ መፍጠር ይገባልም ብለዋል።

አምስተኛው የኢትዮጵያ አካባቢ ጤና አጠባበቅ ባለሙያዎች ማኅበር ዓመታዊ የምርምር ጉባኤ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተካሄደ

ዲ.ዩ፦ ግንቦት 20/2014 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) አምስተኛው የኢትዮጵያ አካባቢ ጤና አጠባበቅ ባለሙያዎች ማህበር ዓመታዊ የምርምር ጉባኤ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተካሄደ።
የምርምር ጉባኤው "በአካባቢ ጤና፣ የድንገተኛ አደጋ ምላሽ እና ተቋማዊ መዋቅር " በሚል መሪ ሀሳብ ላይ አተኩሮ ነው የተዘጋጀው። ዓመታዊ የምርምር ጉባኤውን የኢትዮጵያ አካባቢ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምር እና ስርፀት ዳይሬክቶሬት ጋር በትብብር አዘጋጅተውታል።
በጉባኤው የኢትዮጵያ አካባቢ ጤና ባለሙያዎች ማኅበር ፕሬዝዳንትን ጨምሮ፣ የጤና ሚኒስቴር ኃላፊዎች፣ የአምሪፍ ሔልዝ አፍሪካ ተወካዮች፣ የዩኒቨርሲቲውና የዞን አመራሮች፣ እንዲሁም ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተውጣጡ ተመራማሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

Pages