Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በይፋ ተጀመረ

ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በይፋ ተጀመረ

ለአርሶ አደሮች የቡና ችግኝ ተሰራጨ

ለአርሶ አደሮች የቡና ችግኝ ተሰራጨ

Dilla University and ReWork Inc. Sign MOU to work in collaboration.

Dilla University and ReWork Inc. Sign MOU to work in collaboration.

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

Top News

ዲ.ዩ፤ ሚያዝያ 7/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና እንደሚጫወቱ የተገለጸው የትምህርት ጥራትና ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት “Empowering Academic Advisors Trough Training for Sustainable Quality” በሚል መሪ ሀሳብ ለአማካሪ መምህራን በተሰጠው ስልጠና ላይ ነው ።
ታምራት በየነ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት በመርሃ ግብሩ ባደረጉት ንግግር፤ እየታየ ያለውን የትምህርት ጥራት መጓደል ለማስተካከል እንደ አገር እንዲሁም እንደተቋም ሪፎርም ለማድረግ የተለያዩ ጥረቶች እየተደረጉ እንደሚገኙ ጠቁመው፤ መምህራን በትምህርት፣ በምርምር፣ በስልጠና እንዲሁም ልምድና ተሞክሮዎችን በመለዋወጥ አቅምን ለማሳደግና የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል።
ዶ/ር ታምራት አክለውም፤ የዛሬው ስልጠና አማካሪ መምህራን (Academic Advisors) ተጨማሪ እውቀትና ክህሎት፣ ሙያዊ ልምድ ልውውጥና መነቃቃትን በመጨመር ተማሪዎቻቸውን በቅንነትና በታታሪነት በማገልገል በተቋሙ በሚሰጠው ምዘና ተማሪዎች አጥጋቢ ውጤት እንዲያመጡ፣ በአገር አቀፍ ጀረጃ የሚሰጠውን የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና በብቃት አልፈው በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና እንደሚጫወቱ አስገንዝበዋል ።
በቀለ መንገሻ (ዶ/ር)፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ጥራትና ማሻሻያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ መምህራን የማይተካ ሚናቸውን በአግባቡ እንዲወጡ በማሰብ በሁሉም ኮሌጆች እና ትምህርት ቤቶች የሚገኙ አማካሪ መምህራን በዘርፉ በቂ እውቀትና ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች ለአንድ ቀን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል።
ቸርነት አይተንፍሱ (ዶ/ር)፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ሥነ-ባሕርይ ተቋም መምህርና ተማራማሪ እንዲሁም የእለቱ አሰልጣኝ ስልጠናው የአማካሪ ምንነትና ክህሎት፣ ባሕርይ፣ የተመካሪ ምንነትና ባሕርይ፣ የአማካሪና ተመካሪ ግንኙነት፣ የዩኒቨርስቲው የሴኔት ‘ሌጂስሌሽን’ ስለ አካዳሚክ ማማከር ያስቀመጣቸውን መምሪያና ደንቦች እና ተያያዥ ጉዳዮች፣ ከተሞክሮዎች ጋር በማያያዝ የግንዛቤ ማስጨበጫ መሰጠቱን ገልጸዋል።
በስልጠናው ከታሳፉ መምህራን መካከል መምህር ድረስ ማሞ በሰጡን አስተያየት፤ ከተማሪዎች ጋር ያለውን ግንኙነት ጤናማ በማድረግ እንደ ተቋምና እንደ ሀገር እንዴት ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ተጨማሪ እውቀትና ክህሎት እንዲሁም የህይወት ልምድና ተሞክሮዎችን ያገኙበት ስልጠና መሆኑን ነግረውናል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

gtadmin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *