የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ
ዲ.ዩ፤ መስከረም 23/2017 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በክቡር ፕሬዝዳንቱ የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ቡድን የሰራተኞች ድልድል ኮሚቴ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን ጉብኝት አድርጓል።
ዲ.ዩ፤ መስከረም 23/2017 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በክቡር ፕሬዝዳንቱ የተመራ የከፍተኛ አመራሮች ቡድን የሰራተኞች ድልድል ኮሚቴ እየሰራቸው ያሉ ስራዎችን ጉብኝት አድርጓል።
#Innovative_and_Demand_Driven_Projects_Evaluation_Seminar
ዲ.ዩ፤ መስከረም 15/2017 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ፣ የኢትዮጵያ ሳይንስ አካዳሚ እና ጂ አይ ዜድ (GIZ) ኢትዮጵያ በትብብር ያዘጋጁት የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ስልጠና (Consultation Workshop on Curriculum Framework and Revision of Applied Sciences) ለዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ አመራሮች ተሰጥቷል።
ዲ.ዩ፤ መስከረም 13/2017 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት በዲላ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካማና አካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የደብተር እና የእስኪርብቶ ድግፍ አድርጓል።
ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 30/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት በመሆን ለተሾሙት ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር) የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት እና ካውንስል አባላት በተገኙበት የእንኳን ደህና መጡ የአቀባበል መርሃ-ግብር ተካሂዷል።
ዶ/ር ኤልያስ ዲላ ከተማ ሲገቡ ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር)፣ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ አባል ጨምሮ፣ የዞኑ ካቢኔ አባላት እንዲሁም የቀድሞ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም የጌዴኦ ዞን ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
We are glad to announce a postdoctoral fellowship for one year with a possibility of extension depending on performance and funding.
ዲ.ዩ፦ ነሐሴ 26/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ 2016 የትምህርት ዘመን በበይነ-መረብ እና በወረቀት የተሰጠው ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጀ ማጠናቀቂያ ፈተና በተሰካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ላበረከተው ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እና አስተዋጽዖ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተበረከተለት።
ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 24/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ቡና ምርምር ስልጠና ተቋም በአዋዳ ግብርና ምርምር መለስተኛ ማዕከል ለሰልጣኞች የመስክ ስልጠናና የልምድ ልውውጥ ማድረጉ ታውቋል።
ላለፉት ስድስት ዓመታት ዲላ ዩኒቨርሲቲን በፕሬዚዳንትነት ሲመሩ የነበሩት ዶ/ር ችሮታው አየለ ከነሐሴ 22/2016 ዓ.ም ጀምሮ የሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሁነው እንዲሰሩ በትምህርት ሚኒስቴር ተመድበዋል።