ነጻ የሕግ አገልግሎት ለሚሰጡ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ፤
ዲ.ዩ፤ ታህሳስ 12/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ.)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ት/ቤት ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ከፍተኛ የስደተኞች ኮሚሽን (UNHCR) ጋር በመተባበር በዲላ ዩኒቨርሲቲ ነጻ የሕግ አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ለሚሰሩ የሕግ ባለሙያዎች እና በሕግ ት/ቤት ለሚማሩ የሕግ ተማሪዎች በመሬት ሕግ፣ በውርስ ሕግ፣ በቤተሰብ ሕግና በፍትሐ ብሔር ስነ-ስርዓት ሕግ ላይ ለሦስት ቀናት የቆየ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጥቷል፡፡