Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በይፋ ተጀመረ

ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በይፋ ተጀመረ

ለአርሶ አደሮች የቡና ችግኝ ተሰራጨ

ለአርሶ አደሮች የቡና ችግኝ ተሰራጨ

Dilla University and ReWork Inc. Sign MOU to work in collaboration.

Dilla University and ReWork Inc. Sign MOU to work in collaboration.

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

Top News

ዲ.ዩ፤ የካቲት 16/2016ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የህክምና (Medicine) ትምህርት ክፍልን ጨምሮ በሌሎች አምስት ትምህርት ክፍሎች፣ ከቴክኖሎጂና ምህንድስና ኮሌጅ በኪነ-ህንፃ ምህንድስና (አርክቴክቸር) ትምህርት ክፍል፣ እንዲሁም በተለያዩ የሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ተማሪዎች በዛሬው እለት አስመርቋል።
ታምራት በየነ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፕሬዝዳንቱ ተወካይ ባደረጉት የመግቢያ ንግግር፤ ተመራቂዎች የብዙ እንቅልፍ አልባ ቀናትና ሌሊቶች፣ የብዙ ወራት ልፋቶች እና የብዙ ዓመታት እጅ ያለመስጠት ትግል ውጤቶች ፍሬ አፍርተው ለዛሬ ቀን ደርሳችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ! ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
ይህን የምረቃ በዓል ከሌሎች ጊዜያት እጅግ ለየት የሚያደርገው የጤና ተማሪዎቻችን በሀገር አቀፍ ደረጃ የተዘጋጀውን የመውጫ ፈተና (Exit exam) 99 .9 በመቶ በማምጣት እነሱ ደስ ብሏቸው እኛንም ደስ እንዲለን ያደረጉበት ዕለት ስለሆነ ነው ሲሉ ገልጸው፤ ይህ ውጤት እንደ ተቋም እጅግ በጣም የምንኮራበት ከመሆን ባለፈ መንግስት ጤናን ለዩኒቨርሲቲያችን እንጀ ትኩረት አቅጣጫ ሲሰጥ ትክክል እንደነበር የምናረጋግጥበት ማሳያም ጭምር ነው ሲሉ ዶ/ር ታምራት ተናግረዋል።
ዶ/ር ታምራት አክለውም፤ በቀጣይ ተመራቂዎች በሚሰማሩበት መስክ ሁሉ አምባሳደር ሆነው የዩኒቨርሲቲውን መልካም ስም እንዲያስቀጥሉ የአደራ መልዕክታቸውን ጭምር አስተላልፈዋል።
የእለቱ የክብር እንግዳ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባል ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር፤ “ውድ የዛሬ ተመራቂ ተማሪዎቻችን በተለይም የጤና ተማሪዎች በሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተናው ያመጣችሁት ውጤት እንደ ጌዴኦ ዞንም ሆነ እንደ ዩኒቨርሲቲ እንጅግ የሚያኮራ ስለሆነ ሁላችሁንም እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለው” ብለዋል።
በትምህርት ስርዓት ውስጥ መመረቅ ማለት ቀላል ልፋት አይጠይቅምና ዛሬ በእንደዚህ አይነት ውጤት አምሮባችሁ ለብሳችሁ እዚህ ስትቆሙ ያሳለፋችሁት መንገድ ቀላል አይደለምና እነዚያን የፈተና ጊዜያት በፅናት አልፋችሁ፣ ፈጣሪ ረድቶአችሁና የእናንተም ትጋት ታክሎበት ዛሬ ለዚህ በመብቃታችሁ በድጋሜ ሁላችሁንም እንኳን ደስ አላችሁ ማለት እፈልጋለሁ ሲሉ ዶ/ር ዝናቡ አክለዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋና ለሬጅስትራር አስናቀ ይማም (ዶ/ር) በበኩላቸው፤ በዛሬው ዕለት በቅድመ ምረቃ መርሃ-ግብር 285 ወንድ እና 91 ሴት በድምሩ 376፣ በሁለተኛ ዲግሪ የትምህርት መርሃ-ግብር 48 ወንድ እና 10 ሴት በድምሩ 58፣ በአጠቃላይ 333 ወንድ እና 101 ሴት በድምሩ 434 ተመራቂዎች ለምርቃት መብቃታቸውን አሳውቀዋል።
በዕለቱ የምርቃት ሥነ ሥርዓት ከተመራቂ ተማሪዎች መካከል ከህክምና እና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የፋርማሲ ትምህርት ክፍል ምሩቅ የሆነው አቡሉ ዲሳሳ፣ አጠቃላይ ውጤት 3.98 በማምጣት የዋንጫ እና የሜዳሊያ ተሸላሚ ሲሆን የሚድዋይፈሪ ትምህርት ክፍል ምሩቅ የሆነችው የአብስራ ደምሴ ከሴት ተማሪዎች አጠቃላይ ውጤት 3.89 ነጥብ በማስመዝገብ የዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች።
የምርቃት ስነ-ስርአቱ የህክምና ተመራቂዎች ሙያዊ ቃለ-መሃላ በማስፈጸም የተጠናቀቀ ሲሆን፥ በስነ-ስርአቱ የክብር እንግዶች፣ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ በተለያየ እርከን የሚገኙ የመንግስት ኃላፊዎች፣ የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የባህል ማዕከል ልዩ ልዩ ጣዕመ ዜማዎችን በማቅረብ የዝግጅቱ ድምቀት ሆኗል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram:https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

gtadmin