Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በይፋ ተጀመረ

ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በይፋ ተጀመረ

ለአርሶ አደሮች የቡና ችግኝ ተሰራጨ

ለአርሶ አደሮች የቡና ችግኝ ተሰራጨ

Dilla University and ReWork Inc. Sign MOU to work in collaboration.

Dilla University and ReWork Inc. Sign MOU to work in collaboration.

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

Top News

ዲ.ዩ፤ የካቲት 1/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ እና የጌዴኦ ዞን አስተዳደር በትብብር ያዘጋጁት “ክብር ለአካባቢ ጥበቃ ጀግኖቻችን የጌዴኦ ማሕበረሰብ” በሚል መሪ ቃል የጌዴኦ ብሔር የቋንቋና ባህል- ዳራሮ ሲምፖዚየም ተካሂዷል።
ታምራት በየነ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትና የፕሬዚዳንቱ ተወካይ ባሰሙት የመክፈቻ ንግግር፤ የጌዴኦ ህዝብ የራሱ ባህል፣ ቋንቋ፣ ታሪክ መገለጫ የሆነውን የባሌ ሥርዓት (የገዳ ሥርዓት) ዕሴት፣ ትውፊት እንዲሁም የራሱ የዘመን አቆጣጠር ያለው መሆኑን ጠቁመው፤ ጀግኖች አባቶቻችን ተንከባክበው ያወረሱን ባህላዊ መልከዓ ምድር በዩኔስኮ የተመዘገበበት ዓመት በመሆኑ የዘንድሮው ዳራሮ በዓል ልዩ ድምቀትና ክብር ይሰጠዋል ሲሉም አክለዋል
በዩኔስኮ የተመዘገበው መልከዓ ምድር ወደ ኢኮኖሚያዊ ፈይዳ ለመቀየር እንዲሁም የዳራሮ በአል አከባበርን በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርግ ዶ/ር ታምራት አያይዘው አንስተዋል።
ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት ባስተላለፉት የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት፤ ተፈጥሮን ከሰው ልጅ አስማምተን ለማኖር በትግል ውስጥ ባለንበት ዘመን የጌዴኦ ህዝብ ከሺህ ዓመታት በፊት ሰው ከተፈጥሮ ጋር እንዴት ተስማምቶ መኖር እንደሚችል በማወቅ በትውልድ ቅብብሎሽ ለዚህ ዘመን በማድረስ የዓለም ሻምፒዮን ለመሆን መብቃቱን አውስተው የጌዴኦ ብሔር የባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም ለሰባተኛ ጊዜ መካሄዱን ገልጸዋል።
ዶክተር ሀብታሙ አያይዘውም የጌዴኦ መልክዓ ምድር የዓለም ቅርስ ሁኖ እንዲመዘገብ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አስተውጽኦ ማድረጉን አስታውሰው፣ በቀጣይ ዓመት የሚካሄደውን የዳራሮ ሲምፖዚየም አገር አቀፍ ለማድረግ እቅድ መያዙን አሳውቀዋል።
በሲምፖዚየሙም የተከበሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ ኮሬ ፣ የኢፌዴሪ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባልና የፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢ የእለቱን ቁልፍ መልእክት (keynote) አቅርበዋል። እንዲሁም መምህር ተስፋዬ ገዴቾ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሀገረሰብ ጥናት ተቋም ተመራማሪ በዳራሮ ባህላዊ ስርዓት አከባበር ላይ የጥናት ዳሰሳ ያቀረቡ ሲሆን፤
አብዮት መብራቴ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሀገረሰብ ጥናት ተቋም ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓ ምድር በዩኔስኮ መመዝገቡ የሚያስገኛቸውን እድሎችንና ተግዳሮቶችን በተመለከተ ዳሰሳ አቅርበዋል።
በቀረበው የእለቱ ቁልፍ መልእክት እና የጥናት ዳሰሳዎች ላይ ከመድረኩ ተሳታፊዎች ሐሳብ አስተያየቶች ተነስተው ወይይት የተካሄደባቸው ሲሆን፤ መድረኩን ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር)፣ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ አባል መርተውታል።
ዶ/ር ዝናቡ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር፤ በሲምፖዚየሙ ትኩረት የተደረገባቸው ጉዳዮች የተሰጠንን ፀጋ እንዴት መጠቀም እንዳለብንና የሚገጥሙንን ተግዳሮቶች እንዴት ወደ እድል እንዴት መቀየር እንደምንችል፣ ሀገር በቀል እውቀቶችን ከቴክኖሎጂ ጋር ማስተሳሰር እንደሚገባ እንዲሁም ባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ እንዲኖራቸው አስቻይ ሁኔታዎች ማመቻቸት መሆኑን አስረድተዋል። አያይዘውም፤ ዲላ የዩኒቨርሲቲ እና የጌዴኦ ዞን አስተዳደር የአካባቢውን ማሕበረሰብ ለማገልገልና የሀገርን እድገትን እውን ለማድረግ በከፍተኛ ትብብር በመስራት ላይ እንደሚገኙ ገልጸው፤ በዚህ ረገድ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የጌዴኦ መልክዓ ምድር የዓለም ቅርስ ሁኖ እንዲመዘገብ ላደረገው አስተዋፅኦ ዶ/ር ዝናቡ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የእለቱን ቁልፍ መልእክት ላቀረቡት ለክቡር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ፣ የጥናት ዳሰሳ ላቀረቡት መምህር ተስፋዬ፣ ዶክተር አብዮት እንዲሁም ሲምፖዚየሙ እንዲሳካ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።
በሲምፖዚየሙ የክልል፣ የዞን፣ የወረዳ፣ የዲላ ከተማ አስተዳደር የመንግሥት የስራ ሀላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲው የበላይ አመራሮች፣ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ መምህራን፣ የአስተዳደር ሰራተኞችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ

gtadmin