Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በይፋ ተጀመረ

ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በይፋ ተጀመረ

ለአርሶ አደሮች የቡና ችግኝ ተሰራጨ

ለአርሶ አደሮች የቡና ችግኝ ተሰራጨ

Dilla University and ReWork Inc. Sign MOU to work in collaboration.

Dilla University and ReWork Inc. Sign MOU to work in collaboration.

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

Top News

ዲ.ዩ፤ መጋቢት 26/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ለተማራማሪዎች፣ ለውስጥ ሰራተኞች እና ለባለድርሻ አካላት በቡና ጥራት ቅምሻ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል።
ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዚዳንት በስልጠናው መክፈቻ ባደረጉት ንግግር፤ በቡና ስራ የተሰማሩ አርሶ አደሮች፣ ነጋዴዎች እና ባለድርሻ አካላት ከዘርፉ ተገቢውን ትርፍ እንዲያገኙ፣ የስራ እድልና ሀብት ፈጠራን በማስፋት ለሀገር እድገት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ ዲላ ዩኒቨርሲቲም ቡናን በመማር ማስተማር፣ በምርምር እና በማሕበረሰብ አገልግሎት ስራዎች በማካተት እየሰራ እንደሚገኝ አንስተዋል።
ለተመራማሪዎች፣ ለመምህራን እና ለሰራተኞች የተዘጋጀውን ስልጠና በቀጣይ አጠናክሮ በመቀጠል ያለውን አቅም በማስፋት ዘርፉን የቤተ ሙከራ፣ የተግባር ስራና የምርምር ስራዎች በመስራት የእውቀትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ተግባራዊ የሚሆንበት የልህቀት ማዕከል ለማድረግ ጥረት እንደሚደረግ ዶ/ር ሀብታሙ አያይዘው ገልጸዋል።
አለሙ ደሳ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ ዩኒቨርሲቲው በሀገርና በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያለው ቡና የሚመረትበት አካባቢ የሚገኝ በመሆኑ ለቡና ልማት ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ስራዎች በመከወን ላይ እንደሚገኝ ጠቅሰው ቡና ለሀገራችን የውጭ ምንዛሬ በማስገኘት ለብዙ ሚሊዮን ህዝብ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የገቢ ምንጭ ነው ሲሉ ተናግረዋል።
ይህ ስልጠና በተቋሙ ስር የሚገኙ ተመራማሪዎች፣ ሰራተኞች እና ባለድርሻ አካላት በቡና ጥራት ቅምሻ የተሰጠ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሆኑን ዶ/ር አለሙ አያይዘው ገልጸዋል።
መምህር ኩምሳ ወልደጊዮርጊስ፣ በቡና ምርምርና ስልጠና ተቋም የስልጠና አስተባባሪ፤ የስልጠናው ዓላማ በተቋሙ ስር ያሉ ተመራማሪዎች፣ መምህራንና ሰራተኞች በንድፈ ሀሳብ ደረጃ የሚያውቁትን በተቋሙ ውስጥ በተደራጀው የቡና ጥራት መፈተሻ ቤተሙከራ ውስጥ የቡና ጥራት በቅምሻ በመለየት ተግባራዊ የሆነ እውቀት ለማዳበር መሆኑን አስረድተዋል።
እንደ መምህር ኩምሳ ገለጻ፤ ስልጠናው ከኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዲላ ቅርንጫፍ በዘርፉ በቂ እውቀትና ልምድ ያላቸውን ባለሙያ በመጋበዝ ከንድፈ ሀሳብ ጀምሮ በተግባር የቡና ጥራት በመለየት ዙሪያ ለተከታታይ ሶስት ቀናት ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል።
አቶ ተካልኝ መንገሻ፣ በኢትዮጵያ ምርት ገበያ በዲላ ቅርንጫፍ ጥራት ተቆጣጣሪ፤ በስልጠናው የቡና ጥራት የሚያጓድሉ ሁኔታዎች፣ የቡና ጥራትን እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል፣ ከችግኝ ተከላ ጀምሮ እስከ ቡና ቁሌትና ማፍላት ድረስ ያለውን ሂደት በንድፈ ሀሳብ ተጀምሮ በቤተ ሙከራ በተግባር የተደገፈ በቂ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስልጠና መሰጠቱን ገልጸዋል።
አቶ ተካልኝ አክለው፣ የቡና ምርታማነትን ለማሳደግና የቡና ጥራትን በማስጠበቅ ለአካባቢውና ለሀገር የሚያበረክተውን ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ ከፍ ለማድረግ የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ የጀመረውን ትብብር አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ስልጠናውን ከወሰዱ መምህራን መካከል መምህር ጨምር ጨዋቃ፤ ስልጠናው ተግባር ተኮር የሆነ ከሙያቸውና ከሚሰሩት ምርምር ጋር የሚሄድ ተጨማሪ እውቀትና ክህሎት የሚሰጥ እንደነበር አስተያየታቸውን ሰጥተውናል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

gtadmin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *