አይነስውራን ተማሪዎች ተስማሚ መሠረታዊ የኮምፒውተር ስልጠና (Jaws) እየተሰጠ ነው
ዲ.ዩ የካቲት 30/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የልዩ ፍላጎት ትምህርት ድጋፍ ማዕከል ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በድምጽ አማካኝነት በሚሰጥ ትዕዛዝ ስራዎችን ለማከናወን የሚያስችልና ለአይነስውራን ተስማሚ የሆነ (Job Access With Speech) የኮምፒውተር መተግበሪያ እና የብሬል ማንበብና መጻፍ ክህሎት ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡