Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ መጋቢት 27/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ የመምህራን እና ተመራማሪዎችን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ በምርምር ጽሁፍ ረቂቅ አጻጻፍ፣ በአሳታሚ ምርጫ እና በማሳተም ዙሪያ በሃሴ ዴላ ግቢ ስልጠና ሰጥቷል፡፡
ምስጋኑ ለገሰ (ዶ/ር)፣ የምርምር፣ ህትመት፣ ስነ ምግባርና ሥርፀት ዳይሬክተር፤ በዩኒቨርሲቲው በርካታ ምርምሮች እየተሰሩ መሆኑን ገልጸው፤ ተመራማሪዎች ስራዎቻቸውን እንዴት እውቅና ባላቸው ጆርናሎች በማሳተም ወደ አለም አቀፍ የሳይንስ ማህበረሰብ ማቅረብ ይችላሉ ከዚያም አልፎ የተቋሙን ስም እንዴት ያሳድጋሉ የሚለውን የሚያሳይ ስልጠና እንደሆነ አስረድተዋል፡፡
አቶ ታሪኩ ሎራቶ፣ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን እና የኢኮኖሚክስ ት/ክፍል መምህር በበኩላቸው፤ ኮሌጁ በዩኒቨርሲቲው ካሉ አንጋፋ ኮሌጆች መካከል አንዱ መሆኑን ጠቅሰው፤ በኮሌጁ መምህራን በምርምር ዘርፍ በዩኒቨርሲቲ የሚደገፉ ከ50 በላይ ምርምሮች እየተሰሩ እንደሚገኙና እነዚህ የማህበረሰቡን ችግር የሚፈቱ ጥናቶች አለም አቀፍ ጆርናሎች ላይ መታተም ስላለባቸው የመምህራንን የምርምር ስራዎችን የማሳተም አቅም ለመገንባት ታሳቢ ያደረገ ስልጠና እንደሆነ ተናግረዋል።
ስልጠናውን የወሰዱ በህዝብ አስተዳደር ልማት አመራር ት/ክፍል መምህርት ማህሌት ገ/መስቀል፤ አርቲክሎችን እንዴት ማዘጋጀት እና ማሳተም እንደሚቻል እውቀትና ክህሎት ያገኘሁበት ስልጠና ነበር ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተውናል፡፡
በኢኮኖሚክስ ት/ክፍል መምህር የሆኑት አቶ ጋረደው አወቀ በበኩላቸው፤ ከመማር ማስተማር ጎን ለጎን በምርምር በመሳተፍ የምርምር ስራዎችን የማሳተም ሂደቶች ምንድን ናቸው፣ የምርምር አርቲክል እንዴት ይጻፋል፣ ጥሩ አሳታሚ ጆርናሎችን እንዴት መምረጥ ይቻላል በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ጥሩ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀውልናል፡፡
ከ50 በላይ የሚሆኑ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ መምህራን እና ተመራማሪዎች ስልጠናውን መከታተላቸው ታውቋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et