Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

Top News

ዲ.ዩ፤ ታሕሳስ 17/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከጌዴኦ ዞንና ከአጎራባች ሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳ ለተውጣጡ ወጣቶች በስነ-ተዋልዶ ጤና ዙሪያ ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።

ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር፤ የተቋሙ ዋና ተልዕኮ ማስተማር፣ ምርምር እና የማሕበረሰብ አገልግሎት መሆኑን አስታውሰው ያለውን እምቅ የሰው ሀብትና ውስን በጀት በመጠቀም በበጀት ዓመቱ የተለያዩ ስልጠናዎችን ለመስጠት ዕቅድ በመያዝ ስልጠናዎች እየተሰጡ እንደሆነ አስረድተዋል።

ዶ/ር ሀብታሙ አያይዘውም፤ ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን እውቀትና ክህሎት በየአካባቢያቸው ለሚገኙ ወጣቶችና ማሕበረሰቦች በማካፈል ወደ ተግባር እንዲቀይሩት የማሳሰቢያ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

አቶ ትዛልኝ ተስፋዬ፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ፤ ሀገር ተረካቢ የሆኑ ወጣቶችን በስነ-ተዋልዶ ጤና በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ማድረግ ለነገ የማይባል ስራ መሆኑን ጠቅሰው፤ በስልጠናው የስነ-ተዋልዶ ምንነት፣ የአባላዘር በሽታዎች፣ የቤተሰብ ምጣኔ፣ ያለአቻ ጋብቻና ተያያዥ ጉዳዮች መዳሰሳቸውን አስረድተዋል።

አቶ ተካልኝ ታደሰ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ የማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ከሚሰራቸው አንኳር ተግባራት አንዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሆኑን አስታውሰው፣ በዚህ በዘርፉ በቂ እውቀትና ልምድ ባላቸው የዩኒቨርስቲው ጤናና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን ለሶስት ቀናት ሲሰጥ በነበረው ስልጠና በጌዴኦ ዞን ከሚገኙ ስምንት ወረዳዎችና አምስት ከተማ አስተዳደሮች እንዲሁም ከአጎራባች የሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳ የተውጣጡ ወጣቶች ተሳታፊ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አቶ ተካልኝ አክለውም፣ ስልጠናውን አሳታፊና ተግባር ተኮር በማድረግ እንዲሁም ሰልጣኞች ወደየአካባቢያቸው ሲመለሱ ያገኙትን እውቀትና ግንዛቤ ለሌሎች ወጣቶች የሚያካፉሉበትን እቅድ በማዘጋጀት ዩኒቨርስቲው በቀጣይ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት የሚሰራውን ስራ ለመደገፍና ለመከታተል የሚያስችል ስርዓት ለመዘርጋት ጥረት እየተደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

ከሰልጣኝ ወጣቶች መካከል ቤተልሔም ታደሰና ሙሉቀን አሰፋ በሰጡን አስተያየት፤ በስልጠናው ስለ ስነ-ተዋልዶ ጤና በቂ ግንዛቤ በማግኘታቸው የግል ህይወታቸውን በተሻለ መንገድ ለመምራት እንደሚጠቅማቸው እንዲሁም ለጓደኞቻቸውና ለማህበረሰቡ ግንዛቤ ለመስጠት የሚያስችል ግንዛቤ እንደተፈጠረላቸው ተናግረዋል።

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ

የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ

Telegram: https://t.me/dprd9

Email: pirdir@du.edu.et

p.o.box: 419

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *