Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በይፋ ተጀመረ

ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በይፋ ተጀመረ

ለአርሶ አደሮች የቡና ችግኝ ተሰራጨ

ለአርሶ አደሮች የቡና ችግኝ ተሰራጨ

Dilla University and ReWork Inc. Sign MOU to work in collaboration.

Dilla University and ReWork Inc. Sign MOU to work in collaboration.

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

Top News

ዲ.ዩ፤ ታሕሳስ 19/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት በጌዴኦ ዞን ከሚገኙ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለተወጣጡ የኬሚስትሪ መምህራን በኬሚስትሪ ቨርቹዋል ቤተ ሙከራ ዙርያ ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል።

አቶ ተካልኝ ታደሰ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፣ ለትምህርት ጥራት መሻሻል የሁሉንም ባለድርሻ አካላት ርብርብ እንደሚፈልግ ጠቁመው፤ መረጃዎች እንደሚያሳዩት በዞኑ ከጊዜ ወደ ጊዜ የተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍን የሚመርጡ ተማሪዎች ቁጥር እየቀነሰ መምጣቱን አንስተዋል። ይህን ክፍተት ለማስተካከልና በአጠቃላይ የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ዲላ ዩኒቨርሲቲ የበኩሉን ሚና ለመወጣት የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን በመስጠት ላይ መሆኑንም አስረድተዋል።

ስልጠናውን የወሰዱት መምህራን ያገኙትን እውቀትና ልምድ ወደየትምህርት ቤታቸው ሲመለሱ ተግባር ላይ እንዲያውሉት የአደራ መልእክታቸውን አያይዘው አስተላልፈዋል።

አቶ አለማየሁ ገናታ፣ የጮርሶ ወረዳ ትምህርት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ በበኩላቸው፤ ስልጠናው የዘመኑን ቴክኖሎጂ መሰረት ያደረገ በመሆኑ በትምህርት ቤቶችና በወረዳው የነበረው የቤተ-ሙከራ የግብዓት ችግር በማቃለል የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ እንደሆነ ገልጸዋል። ሰልጣኞችም ከስልጠናው ባገኙት እውቀት በየትምህርት ቤቶች በሚገኙ ኮምፒውተሮች የተለያዩ ሶፍትዌሮችን በመጫን የተለያዩ ሙከራዎችን ለመስራት የሚያስችል አቅም እንደተፈጠረላቸው አውስተው ዲላ ዩኒቨርሲቲ እንዲህ ያሉ ስልጠናዎችን በመስጠት እያደረገ ያለውን እገዛ አመስግነው መሰል ስልጠናዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።

አቶ ብሩህ ተስፋሁን፣ በዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት የአጫጭር ስልጠናዎች አስተባባሪ የማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ከሚሰራቸው አንኳር ተግባራት አንዱ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠት መሆኑን አስታውሰው፤ በኬሚስትሪ ቨርቹዋል ቤተ ሙከራ በቂ እውቀትና ልምድ ባላቸው የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኬሚስትሪ መምህራን ለሶስት ቀናት ሲሰጥ በነበረው ስልጠና ከጌዴኦ ዞን ጮርሶ ክላስተር ከሚገኙ ስድስት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ የኬሚስትሪ መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውን አሳውቀዋል።

አቶ ብሩህ አክለው፤ ስልጠናውን አሳታፊና ተግባር ተኮር በማድረግ ሰልጣኝ መምህራን ወደየትምህርት ቤታቸው ሲመለሱ ያገኙትን እውቀትና ልምድ ለተማሪዎቻቸው የሚያስተምሩበት የሙከራ እቅድ ማዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።

ስልጠናውን ከወሰዱ መምህራን መካከል ትታይ አሸብር እና ጥበቡ ሰለሞን በሰጡን አስተያየት፤ ተማሪዎችን የተለያዩ ሙከራዎችን ለማሰራት ከኬሚካል ጀምሮ ከፍተኛ የሆነ የግብዓት እጥረት ይገጥማቸው እንደነበር ጠቅሰው፤ አሁን በወሰዱት ስልጠና በትምህርት ቤታቸው የሚገኙ ኮምፒውተሮች ላይ የኬሚስትሪ ቨርቹዋል ቤተ ሙከራ ሶፍትዌርን በመጫን ስርዓተ ትምህርቱ የሚያዘውን የተግባር ትምህርት ሁሉ ተማሪዎቻቸውን ለማሰራት የሚያስችል እውቀትና ክህሎት መያዛቸውን ተናግረዋል።

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ

የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ

Telegram: https://t.me/dprd9

Email: pirdir@du.edu.et

p.o.box: 419

gtadmin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *