ዲ.ዩ:- የካቲት 15 /2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ):- ዲላ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ሲያስምራቸው የቆዩ 434 ተማሪዎችን በነገው እለት ያስመርቃል። የዩኒቨርሲተው ሴኔት ጉባዔ በዛሬው እለት ባደረገው ስብሰባ የእጩ ምሩቅ ተማሪዎችን ውጤት አጽድቋል።
የዩኒቨርሲቲው ሴኔት በዛሬው እለት ያፀደቀው ለመመረቅ የሚያበቃቸውን ቅድመ ሁኔታ ያሟሉ እና የመመረቂያ ውጤት ማምጣታቸው የተረጋገጠላቸውን በቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ሲከታሉ የቆዩ 376 ተማሪዎችን እና 58 የድህረ ምረቃ ተማሪዎችን በድምሩ የ434 ተማሪዎችን ውጤት ነው።
እነዚህ ውጤታቸው በሴኔቱ ጉባዔ ተመርምሮ እና ለመመረቅ የሚያበቃቸው ውጤት ማስመዝገባቸው የተረጋገጠላቸው ተማሪዎች በነገው እለት የካቲት 16/2016 ዓ.ም እንዲመረቁ ሴኔቱ አጽድቋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲዲላ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
Facebook: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et




