Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

Top News

ዲ.ዩ፤ ሰኔ 29/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2016 የትምህርት ዘመን ማጠቃለያ የቅድመ 1ኛ ክፍል ተማሪዎችን በዛሬው ዕለት አስመርቋል፡፡
ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኮሚኒቲ ት/ቤት ለዩኒቨርሲቲ መምህራንና አስተዳደር ሠራተኛ ልጆች እንዲሁም ለአካባቢው ማህበረሰብ ጥራት ያለው ትምህርትን ለመስጠት በማለም ከ 2002 ዓ.ም ጀምሮ ለተከታታይ 14 ዓመታት ሲሰራ መቆየቱን ገልጸው፤ ትምህርት ቤቱ ሞዴል እንዲሆን ለማስቻል ዘርፈ ብዙ የትምህርት ጥራትና አግባብነት እንዲሁም ፍትሃዊነትን ለማስጠበቅ የሚያስችሉ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝና ለዚህም የዩኒቨርሲቲው አመራር ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ገቢ ማስገኛ ኢንተርፕራይዝ ዋና ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ የሺ ማሞ፤ የ2016 ዓ.ም የቅድመ 1ኛ ክፍል ተመራቂ ተማሪዎች በትምህርት ዓለም የመጀመሪያ ምዕራፍ ለሆነው ለዚህ ምረቃ ቀን እንኳን አደረሳችሁ በማለት፤ የኮሚኒቲ ት/ቤት እንደ አንድ የገቢ ማስገኛ የኢንተርፕራይዝ አካል በመሆን በ2016 ዓ.ም ወደ ስራ ገብቶ ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት በመስጠት ከሌሎች ት/ቤቶች አንፃር ቀዳሚ ለመሆን እንደሚሰራ ገልጸዋል።
መስፍን ደምሴ (ዶ/ር)፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኮሚኒቲ ት/ቤት ስራ አስኪያጅ፤ በ2016 ዓ.ም አጠቃላይ የት/ት ዘመን አፈፃፀም አቅርበው የኮሚኒቲ ት/ቤት በዲላና አካባቢው ካሉ ት/ቤቶች በትምህርት አሰጣጡም ሆነ እየሰራቸው ባሉ ስራዎች እጅግ ውጤታማ እና ቀዳሚ የሆነ ት/ቤት መሆኑን ገልፀው፤ በ2016 ዓ.ም በተለይ በ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ እንዲሁም በቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት የመማር ማስተማር በተለየ መልኩ ለመፈፀም ታቅዶ ወደ ተግባር የተገባበት እና ከወትሮው ለየት ያለ መሆኑን ገልጸዋል።
ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር)፣ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ በምረቃ መርሃ ግብሩ ላይ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር፤ እንደ አጠቃላይ ህፃናት ላይ የምንሰራው የመማር ማስተማር የሁላችንም ትኩረት የሚፈልግ በመሆኑ ህፃናት ላይ ትኩረት አድርገን ከሰራን ነገ ወላጆቻቸውንም ሆነ ሀገርን መጥቀም የሚችሉ በመሆናቸው የበለጠ መስራት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡
ከቅድመ 1ኛ ደረጃ ት/ቤት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችዉ ተመራቂ ተማሪ ኤፍራታ መልካሙ አጠቃላይ ውጤት 100 ፐርሰንት በማምጣት እንዲሁም ከ1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መካከል ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበችዉ ተመራቂ ተማሪ አዲስ ምስጋና በላይነህ 98.3 ፐርሰንት በማምጣት ተሸላሚ ሆነዋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *