Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Prime News Top News

ዲ.ዩ ግንቦት 14/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ዘርፍ በአቅራቢያው ከሚገኙ የኢንዱስትሪ ተቋማት ጋር በጋራ ለመስራት የመግባቢያ ሰነድ ተፈራርሟል፡፡
የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጅ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ በተለይ በትብብር የሚሰሩ ስራዎች ለዩኒቨርሲቲ- ኢንድስትሪ ተቋማት ግንኙነት ወሳኝ መሆኑን ገልጸው፤ ዩኒቨርሲቲው ከኢንዱስትሪ የሚወስዳቸው ልምድ ያላቸው ባለሙያዎች መኖራቸውን ገልጸው፤ የተፈጠረው ትስስር የሚፈልጋቸውን ክህሎቶች መምህራንን በመላክ ማሰልጠንና ማብቃት እንደሚያስችል ተናግረዋል።
ዶ/ር ሀብታም አያይዘው፤ የዩኒቨርሲቲና የኢንዱስትሪ ትስስርን ማረጋገጥ የምናሰለጥናቸው ተማሪዎች ላይ ያለው ፋይዳ ትልቅ ነው ሲሉ አንስተው፤ ይህንን ለማሳካት ከተቋማት ጋር የመግባቢያ ሰነድ መፈራረም አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን አስገንዝበዋል፡፡ ዩኒቨርሲቲው በተሰጠው የትኩረት አቅጣጫ ላይ ለመስራት የኢንደስትሪው አቅም አስፈላጊ መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል።
አቶ ዳንኤል ተሾመ፣ የቀባዶ ቴክኒክ እና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ዲን በበኩላቸው፤ በከፍተኛ ትምህርት ተቋማትና ቴክኒክና ሙያ ትምህርት ስልጠና ኮሌጆች በጋራ የሚሰሩት ብዙ ስራ እንዳላቸው እና ለዚህም በቴክኒክና ትምህርት ስልጠና ኮሌጅ ፖሊሲ እና እስትራቴጂ ላይ የተቀመጡ የትብብር አይነቶች እንዳሉ ገልጸው፤ የተለያዩ የሙያ ስልጠናዎችን ሲሰጡ የሚኖሩ የክህሎት ክፍተቶችን መሙላት የሚቻለው ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በመተባበር እንደሆነ ተናግረዋል።
አቶ ሀብታሙ አለማየሁ፣ የዲላ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ዲን በተመሳሳይ፤ በዋናነት ዩኒቨርሲቲውና ኮሌጁ በጋራ ተቀናጅተው ለመስራት የሚያግዝ የመግባቢያ ሰነድ መፈራረማቸውን ገልጸው፤ ዩኒቨርሲቲው ያለውን ትልቅ አቅም ተጠቅመን የምርምር እና የቴክኖሎጅ ሽግግር ስራዎችን በጋራ ለመስራት ያግዘናል ሲሉ አስረድተዋል።
የጋራ መግባቢያ ሰነዶቹ የፊርማ ስነ ስረዓትም የሶስቱ ተቋማት የተለያዩ አመራሮች በተገኙበት በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተከናውኗል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et