ዲ.ዩ፤ መጋቢት 20/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ 4ተኛውን ሳምንት የላብራቶሪ ኤግዚብሽን አካሂዷል።
አንተነህ ወጋሶ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ዲን በወቅቱ እንደገለጹት፤ የላብራቶሪ ኤግዚብሽኑ ላለፉት ሦስት ተከታታይ ሳምንታት እየተካሄደ መቀጠሉን ገልጸው፤ በባለፈው ሳምንት በኮሌጁ በተያዘው ማንዋል መሰረት በኤግዚብሽኑ የኮሌጁ የውሃ ሃብት እና መስኖ ምህንድስና ት/ቤት ላብራቶሪዎቻቸውን ማቅረባቸውን ገልጸዋል።
ኤግዚብሽኑ በተመሳሳይ መልኩ በየሳምንቱ የሚካሄድ እንደመሆኑ፤ የዛሬው መርሃ ግብር እንደ ሌሎቹ የትምህርት ክፍሎች በሲቪል ምህንድስና ት/ቤት እና በ COTM የትምህርት ክፍል መከናወኑን ዶ/ር አንተነህ አያይዘው ተናግረዋል ።
እንደ ዶ/ር አንተነህ ገለፃ፤ የኢግዚብሽኑ ዋና ዓላማ የኮሌጅ መምህራንና ተማሪዎች በላብራቶሪዎች ውስጥ ያሉትን አጠቃላይ የላብራቶሪ አይነቶችን እንዲያቁ ለማስቻል እና አንዳንድ ላብራቶሪዎች በካምፓኒው ከተዘጋጀላቸው ውጪ የማስተማሪያ ማንዋል ያልነበራቸው በመሆኑ እነዛን ለማዘጋጀት ማስጀመሪያ ፕሮግራም ጭምር እንደሆነ ገልፀዋል።
ይህ የላብራቶሪ ኤግዚብሽን በሚቀጥሉት ሳምንታት ሲቀጥል ከኮሌጁ የሶስት ትምህርት ክፍሎች ማለትም የምግብ፣ የኪነ ህንፃ ምህንድስና እና የኮምፒውተር ሳይንስ ትምህርት ክፍሎች ኤግዚብሽኑ ላይ ላብራቶሪዎቻቸውን የሚያቀርቡ መሆናቸው ከኮሌጁ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በኤግዚብሽኑ የኮሌጁን ኃላፊ ጨምሮ፣ የትምህርት ቤት ዲኖች፣ የትምህርት ክፍል ኃላፊዎች፣ መምህራን እና ተማሪዎች ተሳትፈዋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et






