ዲ.ዩ፤ መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ከዚህ ቀደም ዲላ ዩኒቨርሲቲ በዶመርሶ የምርምርና የቴክኖሎጂ ሽግግር መንደር ያለማቸውና ምርታማነታቸው በምርምር የተረጋገጠ የእንሰት ዝርያዎችን ለይርጋጨፌ ወረዳ አርሶ አደሮች ማሰራጨቱን መግለጻችን ይታወሳል። በዛሬው እለትም የተሻሻሉ የእንሰት ችግኞች በገደብ ወረዳ ለሚገኙና ችግኞችን የመግዛት አቅም ለሌላቸው አርሶ አደሮች አሰራጭቷል።
ተመስገን እንግዳ (ዶ/ር)፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የኘሬዝዳንት ልዩ አማካሪ፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በከፍተኛ ትኩረት ቡና ላይ እየሰራ መሆኑን አንስተው፣ ከዚህ ጎን ለጎን ለአከባቢው ማህበረሰብ ለምግብነትም ሆነ ለኑሮ ዋስትና ከፍተኛ አስተዋጽኦ ባለው እንሰት ላይም ተገቢውን ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት መሆኑን ተናግረዋል።
እንሰት የማህበረሰቡን የምግብ ዋስትና ለማረጋገጥ ብሎም ድርቅን በመከላከል የመሬት ለምነትን የሚጠብቅ እንደሆነ ዶ/ር ተመስገን አያይዘው ገልጸዋል።
አቶ ተካልኝ ታደሰ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ በአመቱ ሊሰራጭ በዕቅድ የተያዘው 6,200 የእንሰት ችግኝ ስርጭት ሙሉ በሙሉ መሰራጨቱንና እቅዱ መሳካቱን ገልጸዋል።
የጌዴኦ ዞን የመንግስት ረዳት ተጠሪና የብልጽግና ፓርቲ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምህረቱ ተፈራ፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ በዞኑ እየሰራ ለሚገኘው ዘርፈ ብዙ ስራዎች አመስግነው፤ አርሶ አደሮች የተሰራጩትን ችግኞች ለምግብነት ከመጠቀም በዘለለ ለቀጣይ ዝርያቸውን በማባዛት መጠቀም እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል።
የዩኒቨርሲቲ ሆርቲካልቸር ትምህርት ክፍል ኃላፊና ተመራማራ ኑረዲን ሀሰን፤ በገደብ ወረዳ ለ4 ቀበሌያት ከየቀበሌያቱ ለ16 አርሶአደሮች ለእያንዳንዳቸው 35 የተሻሻሉ የእንስት ችግኞች በድምሩ ለ64 አርሶ አደሮች መሰራጨታቸውን እንዲሁም ለአንድ ትምህርት ቤት 100 የእንሰት ችግኞች መበርከቱን ገልጸዋል።
የእንሰት ችግኝ ከተሰጣቸው መካከል ያነጋገርናቸው አቶ አበበ አየለ እና ወ/ሮ ጥሩነሽ በእድሉ ተጠቃሚ በመሆናቸው መደሰታቸውን ገልጸው፤ ዩኒቨርሲቲው ላደረገው የማህበረሰብ ድጋፍ ስራ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et













