Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ሕዳር 30/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የ2016 የትምህርት ዘመን አዲስ ገቢ መደበኛ ተማሪዎችን በሰላም ተቀብሎ አጠናቆ በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች ስነ-ምግባር (ዲሲፕሊን) መመሪያ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱ ተገልጿል።

አቶ ሚልክያስ ኦቶሬ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ፤ ስልጠናው ተማሪዎች በተመደቡበት የሙያ መስክ እንደ ሀገር ብቁ ዜጋ ሆነው እንዳይወጡ የሚያደርጉ የሥነ – ምግባር ግድፈቶችን ለማረም ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል።

የስነ ምግባር መመሪያው ከዚህ ቀደም ሲተገበር የቆየ መሆኑን ያነሱት አቶ ሚልክያስ ኦቶሬ፤ ይህ ስልጠና ወቅቱን ባገናዘበ መልኩ የተለመደውን ሰላማዊ የመማር ማስተማር ስራ ለማሳካት የሚሰጥ ስልጠና እንደሆነ ገልጸዋል።

አቶ አማኑኤል ጌካ፣ የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፈው፤ ባለፉት ቀናት የዩኒቨርሲቲው ማሕበረሰብ፣ የተማሪዎች ሕብረትን ጨምሮ የተለያዩ የተማሪ አደረጃጀቶች፣ የአካባቢውና የፌዴራል ፀጥታ ኃይሎች ባደረጉት የጋራ ትብብር ተማሪዎች ወደ ግቢው በሰላም መግባታቸውን ገልጸዋል።

ስልጠናውን የሰጡት አቶ አዲስ ታምሩ፣ የሕግ ትምህርት ክፍል መምህርና የዩኒቨርሲቲው የሕግ አገልግሎት ዳይሬክተር፤ ስልጠናው በዋነኝነት የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የተማሪዎች የዲሲፕሊን መምሪያና የተቋሙ ሌጅስሌሽንን ታሳቢ በማድረግ የተዘጋጀ እንደሆነ ተናግረው፤ በተቋሙ ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደትን ማስቀጠልን አላማ ያደረገ መሆኑን አጽንኦት ሰጥተው ገልጸዋል።

በስልጠናው ተማሪዎች በግቢ ውስጥ በሚኖራቸው ቆይታ ሊከተሏቸው የሚገቡ የስነ ምግባር መርሆዎች ምን ምን እንደሆኑ፤ እንዲሁም የሥነ ምግባር ግድፈቶች ምን ዓይነት ቅጣት ሊያስከትሉ እንደሚችሉ ተዳሷል።

በስልጠናው የመጀመሪያ አመት ትምህርት ቆይታቸውን በተመለከተ አቶ መንግሥቱ ተሾመ፣ የፍሬሽ ማን ጽህፈት ቤት ዲን ተወካይ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን፤ ምዝገባን፣ ውጤትን፣ መታወቂያን እና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በተመለከተ ደግሞ የዩኒቨርስቲው ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር በአቶ አብርሃም አበበ ለተማሪዎች ገለጻ ተደርጓል።