Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ መጋቢት 11/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ሆስፒታል አዘጋጅነት የምርምር ደረጃን የሚያሳይ የጥናትና ምርምር መረጃ አያያዝና አስተዳደር (Research Data management) እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አውድ በጤናው ዘርፍ ያሉ መርሆዎችን በተመለከተ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ትዝአለኝ ተስፋዬ፤ ኮሌጁ ከጀርመን ግሬፍስዋልድ ዩኒቨርሰቲ (Greifswald) ሁለት ተመራማሪዎች ጋር በተደረገ መግባባት በራሳቸው ፈቃድ በምርምር መረጃ አስተዳደር እና በጤናው ዘርፍ የሰው ሰራሽ አስተውሎት አውዳዊ መርሆዎች ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ገልጸዋል።
ስልጠናው በጤና የምርምር ዘርፍ ቴክኖሎጂ የደረሰበትን ደረጃ የሚያሳይ መሆኑን ጠቅሰው ለሁሉም ትምህርት ክፍል መምህራን እንዲሁም ከሦስተኛ ዲግሪ ተማሪዎች እስከ ጀማሪ ተመራማሪዎች ድረስ ላሉ የአካዳሚክ ስታፎች እየተሰጠ እንደሚገኝ አያይዘው ገልጸዋል።
አቶ ትዝአለኝ አክለውም፤ ከጀርመኑ ግሬፍስዋልድ ዩኒቨርሲቲ የመጡ ተመራማሪዎች ምርምር የሚያካሂዱበት ማዕከል ስላላቸው ይህንን የህክምና ማዕከል ከኛ ሆስፒታል ጋር ለማስተሳሰር ፋይዳ እንደሚኖረውም ጠቁመዋል።
ዶ/ር አትንኩት አላምረው፣ በጀርመን ሀገር ግሬፍስዋልድ ዩኒቨርሲቲ “Post Doctoral ተመራማሪ፣ በጥናትና ምርምር መረጃ አያያዝና አስተዳደር ዙሪያ ስልጠና እየሰጡ ያሉ ሲሆን፣ አቶ ኪሩቤል ብሩክ የሶስተኛ ዲግሪ ተማሪ ሲሆኑ በሰው የሰራሽ አስተውሎት በጤናው ዘርፍ በሚል ርዕስ ስልጠና እንደሚሰጡ ለማወቅ ተችሏል።
በስልጠናው ከ20 በላይ የሚሆኑ መምህራን፣ ተመራማሪዎች እንዲሁም የ3ኛ ዲግሪ ተማሪዎች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et