ዲ.ዩ፤ ሰኔ 24/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በጌዴኦ ዞን በኦንላይን ለሚፈተኑ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀ ሞዴል ፈተና በዛሬው ዕለት በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተሰጥቷል።
አቶ ዮናስ ተጠምቀ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ልዩ ረዳት፤ ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለመጀመሪያ ጊዜ በሁለት መልኩ በወረቀትና በኦንላይን እንደሚሰጥ ገልጸው፤ በኦንላይን ለሚፈተኑ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኮሚኒቲ ትምህርት ቤት፣ ዶንቦስኮ እና ዳማ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተፈታኞች በማሕበራዊ ሳይንስ ዘርፍ 424 ተማሪዎች በጠዋት መርሐ ግብር እንዲሁም በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ 187 ተማሪዎች በከሰዓት መርሐ ግብር በአጠቃላይ 611 ተማሪዎች ሞዴል ፈተናውን በተሳካ ሁኔታ መውሰዳቸውን ገልጸዋል።
አቶ በቀለ ወርቁ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አይ.ሲ.ቲ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ ባለፉት ዓመታት በኦንላይን የሚሰጡ ፈተናዎችን በመስጠት በቂ የቴክኖሎጂና የሰው አቅም መገንባቱን ጠቁመው፤ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ተፈታኞች ዩኒቨርሲቲው ያዘጋጀውን አንደኛውን ዙር ፈተና ወስደው ከፈተናው ስርዓት ትውውቅ አድርገው በዛሬው እለት ደግሞ በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀውን ሞዴል ፈተና በአግባቡ ሰርተው በቀጣይ ለሚሰጠው አገር አቀፍ ፈተና በቂ ልምድ ማግኘታቸውን ገልጸዋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et





