Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

Top News

ዲ.ዩ፤ የካቲት 06/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ.ም አጋማሽ ላይ ከየካቲት 6 -11 የሚሰጠውን አገር አቀፍ የመውጫ ፈተና በዛሬው እለት መስጠት ጀምሯል።
ታምራት በየነ (ዶ/ር )፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንትና የፕሬዝዳንቱ ተወካይ፤ በዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ በ2016 ዓ.ም አጋማሽ ላይ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና እንደ ተቋም በተሳካ ሁኔታ ለማካሄድ ሰፊ ቅድመ ዝግጅቶች መደረጋቸውን ተናግረዋል።
ዶ/ር ታምራት አያይዘውም፤ በመውጫ ፈተናው ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት 393 የዲላ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ተመራቂዎች፣ 457 ከግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የመጡ እጩ ተመራቂዎች እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈትነው ዘንድሮ ዳግም የሚፈተኑ 206 ተማሪዎች፤ በአጠቃላይ 1057 እጩ ምሩቃን እስከ የካቲት 11 ድረስ የመውጫ ፈተናውን እንደሚወስዱ ገልጸዋል።
ለዚህም በዩኒቨርሲቲው አብይ ግብረ ኃይል እና ንዑሳን ግብረ ኃይሎች ተቋቁምው ወደ ስራ በመግባት ፈተናውን በአግባቡ ለመስጠት የሚያስችሉ ተግባራትን በማከናውን በፎረሞች ጭምር በማስገምገም ስራዎች ሲከናወኑ መቆየታቸውን ዶ/ር ታምራት ተናግረዋል።
እንደ ዶ/ር ታምራት ገለፃ፤ በዩኒቨርሲቲው በመደበኝነት ለሚፈተኑ ተማሪዎች ትምህርት ሚኒስቴር ከሰጠው የሞዴል ፈተና ባሻገር ተማሪዎች የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ለማስቻል የተለያየ የማካካሻ ትምህርት (Tutorial) እንዲሁም እስከ 3 የሚደርሱ የሞዴል ፈተናዎች እንዲወስዱ መደረጉ ታውቋል።
በዩኒቨርሲቲው የአይ ሲቲ ዳይሬክተር መ/ር በቀለ ወርቁ በበኩላቸው፤ የመውጫ ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲሰጥ አጠቃላይ የኮምፒተር፣ የኔትወርክና ሌሎች አስፈላጊ መሰረተ ልማቶች በበቂ ሁኔታ መሟላታቸውን ጠቁመው፤ ለዚህም በዋናው ግቢ ላይ መጠባበቂያ ክፍሎችን ጨምሮ በእያንዳንዳቸው 22 ኮምፒተሮችን የሚይዙ 14 የመፈተኛ ክፍሎች መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል።
መ/ር በቀለ አክለውም፤ ይህ የመውጫ ፈተና የሚሰጠው አሁን ላይ በዋናው (ኦዳያአ) ግቢ ላይ ብቻ ቢሆንም ምናልባት ከተማሪ ቁጥር ጋር ተያይዞ አንዳንድ መጨናነቆች ቢፈጠሩ ለመጠባበቂያ በቀድሞ ዋና ግቢ ላይ ተማሪዎችን መፈተን የሚያስችሉ 5 የመፈተኛ ቦታዎች ዝግጁ መደረጋቸውን ተናግረዋል።
ፈተናውን ለሚወስዱ አጠቃላይ ተማሪዎች ዲላ ዩኒቨርሲቲ መልካም ምኞቱን ይገልጻል።