Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በይፋ ተጀመረ

ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በይፋ ተጀመረ

ለአርሶ አደሮች የቡና ችግኝ ተሰራጨ

ለአርሶ አደሮች የቡና ችግኝ ተሰራጨ

Dilla University and ReWork Inc. Sign MOU to work in collaboration.

Dilla University and ReWork Inc. Sign MOU to work in collaboration.

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

Top News

ዲ.ዩ፤ ሚያዚያ 18/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በጌዴኦ ዞን ለሚገኙና በዘንድሮ አመት ብሔራዊ ፈተና ለሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠውን የማጠናከሪያ ትምህርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት በይፋ አስጀምሯል።
በማጠናከሪያ ትምህርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ በሀሴሀሮ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዶ/ር ችሮታው አየለ፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት የባዮሎጂ ትምህርት በማስተማር፤ ዶ/ር ታምራት በየነ፤ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንት የኢኮኖሚክስ ትምህርት በማስተማር፤ በጮርሶ ማዞሪያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደግሞ ዶ/ር ደረጄ ክፍሌ፤ የሃሴዴላ ግቢ ኤክስኪዩቲቭ ዳይሬክተር እና ዶ/ር ወንደወሰን ገበየሁ፤ የተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን የሒሳብ ትምህርት በማስተማር አርአያነታቸውን አሳይተዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ችሮታው አየለ (ዶ/ር) እንደገለጹት፤ ዩኒቨርሲቲው አሁን ላይ የትምህርት ጥራት ችግርን ለመቅረፍ በርካታ ስራዎችን እየሰራ እንደሚገኝ አውስተው፤ ከእነዚህም መካከል በዞኑ የሚገኙ የ1ኛ ደረጃ እና የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች የማሻሻል ስራ ላይ የሚውል ህንጻዎችን ጭምር በመስራት ግብአቶችን አሟልቶ ለማስረከብ ሂደት ላይ መሆኑን ተናግረዋል።
በዛሬው ዕለትም ዩኒቨርሲቲው በበጎ ፍቃድ መምህራን በተለያዩ የ2ተኛ ደረጃ ት/ቤቶች ለሚገኙ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት በመስጠት መምህራንና ትምህርት ቤቶችን ለማገዝ ይህን ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ማከናወኑንን ዶ/ር ችሮታው ገልጸዋል።
እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለጻ፤ ይህ የማጠናከሪያ ትምህርት ተማሪዎች በያዙት ዕውቀት ላይ በሚያገኙት የማጠናከሪያ ትምህርት ድጋፍ የበለጠ አሻሽለው የሚፈለገውን ውጤት ማስመዝገብ እንዲችሉ ያለመ መሆኑን አስገንዝበዋል።
ታምራት በየነ (ዶ/ር )፣ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት በበኩላቸው፤ ይህ መርሃ ግብር እንደ ጌዴኦ ዞን ከዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ማነስ ጋር ተያይዞ ያለውን ክፍተት በቅርበት ለማገዝ ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ መርሃ ግብር መሆኑን ተናግረዋል።
በቀጣይም ዩኒቨርሲቲው ይህን ስራ እንደ ጅማሮ በመውሰድ እንደ ሀገርም ሆነ እንደ ዞን ብቁ ዜጋ ለማፍራት እየተደረገ ያለውን ጥረት ለማገዝ በዞኑ ከሚገኙ ከ2ተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ጋር በቅርበት በመስራት ክፍተቶችን ለመሙላት በቁርጠኝት እንደሚሰሩ ዶ/ር ታምራት ተናግረዋል።
በዲላ ዩኒቨርሲቲ የትምህት እና ስነ-ባህሪ ተቋም ዲን ተባባሪ ፕሮፌሰር ዶ/ር መስፍን ሞላ፤ በዞኑ ከሚገኙ የ2ኛ ደረጃ ት/ቤቶች መካከል 5 ትምህርት ቤቶች ላለፉት ሶስት አመታት ምንም አይነት ተማሪ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ባለማስመዝገባቸው ምክንያት ተቋሙ ባጠናው ጥናት መነሻነት በሁሉም ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለመተግበር የማይቻል በመሆኑ ከአምስቱ ውስጥ ሁለት ትምህርት ቤቶችን እንደ ሞዴል በመውስድ ከጥናቱ ውስጥ የአጭር ጊዜ ዕቅድ የሆነውን ይህን የተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት በዛሬው ዕለት ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ መከናወኑን ተናግረዋል።
ዶ/ር መስፍን አያይዘውም፤ በቀጣይም ዩኒቨርሲቲው ከትምህርት ጥራት ጋር ተያይዞ በጥናቱ የተካተቱት የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ የጥናት ዕቅዶች ተግባራዊ እንዲሆኑና በትኩረት ሊሰራባቸው እንደሚገባ ተናግረዋል።
የወናጎ ወረዳ አስተዳዳሪ አቶ አበበ እጅጉ በበኩላቸው፤ መርሃ ግብሩ የተካሄደበት የሀሴ ሀሮ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ያለበትን ክፍተት ለመሙላት ዩኒቨርሲቲው በጎ ፍቃደኛ መምህራንን በመያዝ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የማጠናከሪያ ትምህርት ለመስጠት የማስጀመሪያ መርሃ ግብር በማከናወኑ ምስጋናቸውን በወረዳው ስም አቅርበዋል።
የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ የመምህራን ልማት ዳይሬክተር እና የመምሪያው ኃላፊ ተወካይ የሆኑት አቶ ንፁህ ከበደ በበኩላቸው፤ ከ12ኛ ክፍል ውጤት ጋር ተያይዞ በዞኑ ጥራት ያለው ትምህርት በመስጠት የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ዩኒቨርሲቲው ይህን ፕሮግራም በሌሎች ት/ቤቶች ላይም በማስፋት ተጨባጭ ለውጥ ለማምጣት የበኩሉን ሚና እንዲወጣ አሳስበዋል።
በተያያዘ ዜና ይህ ለ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት ፕሮግራም በጮርሶ ማዞርያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም ተጀምሯል።
በጮርሶ ማዞሪያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የማጠናከሪያ ትምህርት ማስጀመሪያ መርሃ ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ኘሬዝዳንት ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)፤ እንደ ሀገር እየታየ ያለው የተማሪዎች ውጤት ማሽቆልቆል አሳሳቢ ደረጃ የደረሰ በመሆኑ ለበርካታ አመታት ተማሪዎችን አስተምረው ተማሪዎችን ወደ ዩኒቨርሲቲ መላክ ያልቻሉ ትምህርት ቤቶች በጥናት በመለየት በበጎ ፍቃድ አገልግሎት ተማሪዎችን በመደገፍ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ታስቦ የተዘጋጀ እንደሆነ ገልጸዋል።
የጌዴኦ ዞን ትምህርት መምሪያ ኃላፊ ተወካይ በበኩለቸው፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ማህበረሰቡን ክፍተት በጥናት በመለየት ክፍተቱን ለመሙላት የበኩሉን ድርሻ ለመወጣት ይህንን ፕሮግራም ማዘጋጀቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸዋል።
ይህ ለአንድ ወር ከአንድ ሳምንት የሚቆይ ሲሆን በተመረጡት ት/ቤቶች ውስጥ በሳምንቱ የመጨረሻ ቀናት ማለትም አርብ፣ ቅዳሜ እሁድ የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል።
የማጠናከሪያ ትምህርቱን ሲወስዱ ያገኘናቸው ከሀሴ ሀሮ ትምህርት ቤት ተማሪ ታሪኩ ማርያም እና ተማሪ በቀለች ወላሶ፤ እንዲሁም ከጩርሶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ዘመድ፤ የማጠናከሪያ ትምህርት እድል በማግኘታቸው መደሰታቸውን ገልጸው፤ የማጠናከሪያ ትምህርቱ ለተፈታኝ ተማሪዎች ጥሩ መነቃቃትን የሚፈጥር እና ለተሻለ ውጤት የሚያዘጋጅ መሆኑን ገልጸውልናል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

gtadmin