Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ መጋቢት 19/2016 (ህ.ዓ.ግ)፦ 13ኛው አገር አቀፍ ዓመታዊ የምርምር ጉበኤ“ምርምር ለማህበረሰብ ለውጥ” በሚል ዋና ጭብጥ
በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል። የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት እና የምርምር፣ ህትመት፣ ሥነ ምግባርና ሥርፀት ዳይሬክቶሬት ጉባኤውን አሰናድተውታል።
ታምራት በየነ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፕሬዝዳንቱ ተወካይ፤ በመክፈቻ ንግግራቸው ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች የተውጣጡ ምሁራን ምርምራቸውን ማቅረባቸው ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል።
ዶ/ር ታምራት አክለውም፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ መጠን በዚህ ረገድ አተኩሮ እየሰራ መሆኑንና በተለይ ምሁራን የምርምርና ፕሮጀክት ስራዎች ላይ በጥልቀት ገብተው በተግባር የአገሪቱን ችግሮች ሊፈቱ የሚችሉ እንዲሆኑ ታስቦ እየተሰራ መሆኑን አስረድተዋል።
ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት በበኩላቸው፤ 13ኛው አገር አቀፍ አመታዊ የምርምር ጉባኤ መካሄዱ ብዙ ልምዶችን ይዘው የመጡ ተመራማሪዎች በአንድ መድረክ መገናኘታቸው ለልምድ ልውውጥና በቀጣይ አብሮ ለመስራት ወሳኝ እንደሆነ አንስተዋል።
ይህ የምርምር ጉባኤ የዩኒቨርሲቲው ጀማሪ ተመራማሪዎች ልምድ እንዲያገኙ የሚያስችላቸው ብሎም በትብብር ለመስራትና ትውውቅ ለመፍጠር የሚያግዛቸው መሆኑን አያይዘው ገልጸዋል።
ምስጋኑ ለገሰ (ዶ/ር)፣ የምርምር ህትመት ስነ ምግባርና ሥርፀት ዳይሬክተር፤ እንደዚህ አይነት የምርምር ጉባኤዎች ሀገራዊ ፋይዳቸው ትልቅ መሆኑን አንስተው፤ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተገኙ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን አቀናጅቶ በአንድ ፕላትፎርም ማምጣት ለማህበረሰብ ለውጥ ጉልህ ድርሻ እንዳለው ገልጸው በዚህ የምርምር ጉባኤ አርባ የምርምር ስራዎች ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በመጡ ተመራማሪዎች እንደቀረቡ አስረድተዋል።
በጉባኤው ቁልፍ መልዕክት ያቀረቡት አትንኩት አላምረው (ዶ/ር)፣ በጀርመን ግሪፍስ ዋልድ ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪና የ”Post doctoral” ተማሪ በምርምር ዳታ አስተዳደር ዙሪያ ዓለም አቀፋዊ ልምዳቸውን ለተሳታፊዎች አካፍለዋል።
በጉባኤው መክፈቻ መርሃግብር ላይም አብዮት ታደሰ (ዶ/ር)፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ጂኦግራፊ ትምህርት ክፍል መምህርና ተመራማሪ “Social-ecological system in transition understanding the dynamics of Konso cultural landscape UNESCO listed world heritage site” በሚል ርዕስ የምርምር ስራቸውን አቅርበዋል፡፡
በቀጣይም በስድስት የተለያዩ ቦታዎች የተለያዩ የምርምር ስራዎች የቀረቡ ሲሆን በቀረቡ የምርምር ስራዎች ላይ ሐሳብ አስተያየት እንዲሁም ጥያቄዎች ቀርበው ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
በጉባኤው ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተጋበዙ ምሁራን፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ መምህራን፣ ተመራማሪዎች፣ የአካባቢው ማህበረሰብ ተወካዮች እና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል፡፡
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et