ዲ.ዩ (ህ.ዓ.ግ)፦ 29/12/2016 ዓ.ም ኤልያስ አለሙ (ዶ/ር) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ዲላ ከተማ ገብተዋል።
በአቀባበሉ ላይ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት ያስተላለፉት ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር)፣ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ አባል፣ ወደ አረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ እና በአገር በቀል እውቀቱ ከተፈጥሮ ጋር ተስማምቶ መኖር እንዴት እንደሚቻል ለዓለም ወዳሳየው ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ እንኳን ደህና መጡ ብለዋል።
ዶ/ር ዝናቡ አክለውም፣ ዩኒቨርሲቲው የዞኑን ማህበረሰብ አኗኗር ለማሻሻል በርካታ የማህበረሰብ አቀፍ ስራዎችን ሲሰራ እንደቆየ አስታውሰው ባለፉት ዓመታት ሰላማዊ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲኖር ከፍተኛ አስተዋጽኦ ላበረከቱት ዶ/ር ችሮታው አየለ ምስጋናቸው አቅርበው በቀጣይም እንደ አገር የመጡ የሪፎርም ለውጦችን ለማስቀጠል ዞኑ ከዩኒቨርሲቲው ጋር በቅርበት እንደሚሰራ ገልጸዋል።
አያይዘውም በቀድሞ አመራር የተጀመሩ ስራዎችን አዲስ ከተመደቡት ፕሬዚዳንት ጋርም እጅግ በተጠናከረ መንገድ ይዘን እናስቀጥላለን ሲሉ ተናግረዋል።
ዶ/ር ኤልያስ በነገው እለት በዲላ ዩኒቨርሲቲ ማኔጅመንት አባላት እና የዩኒቨርሲቲ ካውንስል አባላት አቀባበል ይደረግላቸውና የትምህርት ሚኒስቴር ተወካዮች እና የማኔጂመንት አባላት ባሉበት ከዶ/ር ችሮታው አየለ ጋር የኃላፊነት ርክክብ ያደርጋሉ።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram:https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et