Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

Top News

ዲ.ዩ፤ ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከስፔን የካታሎንያን ግዛት ጋቫ የስፖርት ትምህርት እና የሴቶች ልማት ማህበር ጋር በመተባበር ኢንተርናሽናል የቅርጫት ኳስ የሙያ ማሻሻያ ስልጠና መስጠቱ ተገልጿል፡፡
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክተር፣ አቶ ተካልኝ ታደሰ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ ከስፔን የካታሎንያን ግዛት ጋቫ የስፖርት ትምህርት እና የሴቶች ልማት ማህበር ጋር ለሁለት ዓመት የሚቆይ የጋራ መግባቢያ መፈረሙን ጠቅሰው፤ ስልጠናው የዚህ የጋራ መግባቢያ ስምምነት አንዱ አካል መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ ተካልኝ አክለውም፤ በስምምነቱ መነሻነት የስፖርት ትጥቅ ድጋፍ ለማድረግ እና የሙያ ማሻሻያ ስልጠና ለመስጠት ከስፔን የካታሎንያን ግዛት ጋቫ የስፖርት ትምህርት እና የሴቶች ልማት ማህበር ባለሙያዎች መምጣታቸውን ገልፀው፤ እንዲህ አይነት የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችን ለመስጠት ከሌሎች ተቋማት ጋር መቀናጀት አስፈላጊ በመሆኑ ቀጣይነቱ ለዩኒቨርሲቲውና ለአካባቢው ማህበረሰብ ትልቅ ፋይዳ እንዳለው አንስተዋል።
ማስረሻ ኢራጎ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት ክፍል መምህርና የፕሮጀክቱ አስተባባሪ በበኩላቸው፤ ይህን ስልጠና አለም አቀፍ የስፖርት ሳይንሰ ባለሙያዎች የሙያ ማሻሻያ ስልጠና መሆኑን ገልፀው፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከስፔን ካታሎንያን ግዛት ጋቫ የስፖርት ማህበር ጋር በመተባበር ስልጠና ከመስጠት ባለፈ የተለያዩ የስፖርት ትጥቆችና ቁሳቁሶችን(የቅርጫት፣ የእጅ፣ የመረብ ኳሶችን፤ ለቅርጫት ኳስ ሰልጣኞች ለሴቶች 30 ለወንዶች 70 ለስፖርት ሳይንስ መምህራኖች 20 ቲሸርትና ቁምጣዎችን እንዲሁም ለማናጅመንት ስታፍም 15 የሚሆኑ ዘመናዊ ቱታዎችን እና የተለያዩ የስፖርት ማቴሪያሎችን ድጋፍ ማድረጋቸው ገልጸዋል።
የስፔን ካታላን የስፖርትና የትምህርት ልማት ማህበር ፕሬዝዳንት ፍራንሲስኮ ጃቪ (Fransisco Javie) እንደገለጹት፤ ይህ ማህበር በተለይ በቅርጫት ኳስ ስፖርት ዕድገት ላይ ከፍተኛ ሥራ የሚሰራና ከኢትዮጵያ ቅርጫት ኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመሆን በኢትዮጵያ ውስጥ በቅርጫት ኳስ ዘርፍ በታዳጊ ወጣቶች ላይ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው፤ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደግሞ ለመጀመሪያ ጊዜ ከዲላ ዩኒቨርሲቲ ጋር ለመስራት ስምምነት ተፈራርሞ ስራ መጀመሩን ተናግረዋል።
በስልጠናው የመዝጊያ ንግግር ያደረጉት አዲሱ ፍሪንጆ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የኢንዱስትሪ ትስስርና የቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር እንዲሁም የምር/ቴክ/ሽ/ምክትል ፕሬዝዳንትን ተወካይ፤ እንደ ዩኒቨርሲቲ ከውጪ እና አገር ውስጥ ካሉ የተለያዩ ድርጅቶች ጋር በጋራ እየተሰራ መሆኑን ገልጸው፤ ዩኒቨርሲቲዎች ስራቸውን ውጭ ካሉ ኢንዱስትሪዎች ጋር ለመስራት የሚፈጥሯቸው ግንኙነቶች ተቋሙን ከማሳደግ ባለፈ ማህበረሰባዊ ጠቀሜታ እንዳላቸው ገልጸዋል።
ከሰልጣኞች መካከል አቶ ተሻለ ዮሴፍ፣ የዲላ ከተማ የስፖርት ትምህርት ስልጠናና ውድድር የስራ ሂደት አስተባባሪ፤ ስልጠናው በቅርጫት ኮስ ዘርፍ ስራ ላይ ላሉትና መስራት ለሚፈልጉ ታዳጊ ፕሮጀክቶች ልማት ላይ እንዴት በምን አይነት ቦታ መሰልጠን እንዳለባቸው ግንዛቤ ያገኙበት ስልጠና መሆኑን ገልጸዋል።
ከጌዴኦ ዞን ወጣቶችና ስፖርት መምሪያ የስፖርት አደረጃጀት ፋሲሊቲ ልማት ቡድን መሪ፣ ሂሩት ደራሮ በበኩላቸው፤ እንደ ዞን ብሎም እንደ ክልል በስፖርት ባለሙያ በቢሮ ደረጃ ስልጠና አግኝተው አለማወቃቸውን ገልጸው፤ ለቀጣይ አደረጃጀት ላይ ከዩኒቨርሲቲውም ጋር በጋራ መስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ግንዛቤ ያገኙበት ስልጠና እንደነበር ገልፀዋል።
በስልጠናው ላይ ከጌዴኦ ዞን ስፖርት ጽ/ቤት፣ ከአጎራባች ዞንና ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የተውጣጡ 50 የስፖርት ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን፤ በስልጠናው ላይ ለተሳተፉ ሰልጣኞች የምስክር ወረቀት ተሰጥቷቸዋል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


ለወቅታዊ መረጃዎች
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: pirdir@du.edu.et

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *