Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

ዲ.ዩ፤ ነሐሴ 17/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ያለው “የምትተክል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ” የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር የችግኝ ተከላ በዲላ ዩኒቨርሲቲ በአራቱም ግቢዎች ከማለዳ ጀምሮ ተከናውኗል፡፡

ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዛሬ በሀገር አቀፍ ደረጃ 600 ሚሊዮን ችግኞችን በአንድ ጀንበር ለመትከል እንደ ሀገር እቅድ ተይዞ እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልፀው፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብም ይህንን ዕቅድ ለማሳካት በአራቱም ግቢዎች የአረንጓዴ አሻራ የማኖር ስራ ማከናዎናቸውን ገልጸዋል።

በአራቱም ግቢዎች ከፍተኛ አመራሩም የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ተከፋፍሎ ችግኞች መተከሉን እና በቅርቡ ከፍተኛ ቁጥር ያለው የቡና ችግኝ ተሰራጭቶ መተከሉንም ፕሬዝዳንቱ አያይዘው ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቱ አክለውም አረንጓዴ አሻራ ማኖር ትልቅ የሀገር ዕቅድ መሆኑን በመጥቀስ እንደ ሀገር ያለንን የአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭነት ለመቀነስ እንዲሁም ምርታማነትን ለማሳደግ የደን ሽፋናችንን ለማሳደግ መንግስት የወጠነውን ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረገ የራሳችንን አስተዋጽኦ እያበረከትን የምንቀጥል ይሆናል ሲሉ ተደምጠዋል።

በተመሳሳይ ከጠዋቱ 1 ሰዓት ጀምሮ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብና ከፍተኛ አመራሮች ከጌዴኦ ዞን አስተዳደር ጋር በመሆን በወናጎ ከተማ ችግኝ የመትከል ስነ ስርዓት አከናውኗል።

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ም/ኘሬዝዳንት ሀብታሙ ተመስገን (ዶ/ር)፤ ዩኒቨርሲቲው ከሚታወቅበት መገለጫ አንጻር አረንጓዴ አሻራ ላይ ያለው ትኩረት ትልቅ መሆኑን ገልፀው፤ ይህ መርሃ ግብር ከመጀመሩ በፊትም ተቋሙ በዞኑም ሆነ በአካባቢው በቡናም ሆነ በምግብ ሰብሎች ላይ ሰፊ ስራ እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

ተመስገን እንግዳ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ፤ ዛሬ እንደ ሀገር የምንተክለው የዛፍ ችግኞች ከመትከል ባለፈ ችግኞችን እንዲጸድቁና እንዲያድጉ መንከባከብ ላይ ትኩረት መስጠት እንደሚያስፈልግ ተናግረዋል።

የፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ መሳይ ፍቅሩ፣ ዩኒቨርሲቲው ከዞኑም ሆነ ከአካባቢው ማህበረሰብ ጋር ያለውን አንድነትና ትብብር ያሳየ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር መሆኑን በማንሳት፤ በቀጣይ የአካባቢውን ስነ ምህዳር ለመጠበቅም ሆነ ለማስጠበቅ በርካታ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚገኙና እንደሚሰሩ ገልጸዋል።

በዕለቱ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ላይ ሲሳተፉ ያገኘናቸው የዲላ ዩኒቨርሰቲ የተማሪዎች አገልግሎት ዳይሬክተር አቶ አንዋር ከድር፤ እንዲሁም የዲላ ዩኒቨርሲቲ የከፍተኛ የገበያ ጥናት ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ ብዙነሽ ቦጬ በሰጡን አስተያየት፤ በሀገራችን እየጋጠሙ ያሉትን በርካታ ሰው ሰራሽና የተፈጥሮ አደጋዎችንና የአየር ንብረት መዛባትን ለመቀነስ እንደ ሀገር የተያዘው አረንጓዴ አሻራ አካል በመሆናቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጸዋል።

በመርሃ ግብሩ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችና የየዘርፉ ኃላፊዎች፣ ሠራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

ዲላ፤

የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et

Telegram:https://t.me/dprd9

website: https://www.du.edu.et

Email: https://www.pirdir@du.edu.et