ዲ.ዩ ነሐሴ 23/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ምርታማነታቸው የተረጋገጡ ‘ቦቫንስ ብራውን’ (Bovans Brown) የተሰኙ እንቁላል ጣይ ዶሮዎችን በማምጣት እያራባ እንደሚገኝ ገለጸ።
ሳምሶን ሀ/ማርያም (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ተወካይ ዲን፤ እንደገለጹት ዲላ ዩኒቨርሲቲ የአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ መጠን ተማሪዎችን በተግባር ለማስተማር ያስችለው ዘንድ ከዚህ በፊትም የተለያዩ ዝርያ ያላቸው ዶሮዎችን ሲያረባ የቆየ ሲሆን፤ አሁን ላይ በእንቁላል ምርታቸው የተሻሉ ቦቫንስ ብራውን የተሰኙ የእንቁላል ጣይ ዶሮ ዝርያዎች አምጥቶ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
ዶ/ር ሳምሶን አክለውም፤ አሁን ላይ ጫጩቶችን ከገበያ እየገዙ መሆኑን ገልፀው፤ በቀጣይ 10,000 (አስር ሺህ) ጫጩቶችን ማስፈልፈል የሚያስችል እንኩቨተር ግዥ መታቀዱን በመግለፅ ለጫጩቶች ማቆያና መመገቢያ ያለው ዘመናዊ የዶሮ ማርቢያ ስፍራ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል።
አቶ መለሰ ምትኩ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ የእንስሳት ዩኒት ፋርም አስተባባሪ በበኩላቸው፤ አሁን ላይ የገቡት ዶሮዎች በእንቁላል ምርታቸው የተሻሉ መሆናቸው የተረጋገጠ የ 85 (ሰማኒያ አምስት) ቀናት 1,500 ዶሮዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram:https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et





