Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ሰኔ 27/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለመማሪያ ክፍል እና ለቢሮ አገልግሎት እንዲውል በአጼ ዳዊት ትምህርት ቤት ውስጥ ያስገነባውን ሕንጻ በዛሬው እለት አስረክቧል።
ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በርክክብ መርሐ ግብሩ ባደረጉት ንግግር፤ መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከሚያደርጋቸው ጥረቶች አንዱ የሆነው የትምህርት ቤቶችን ስታንዳርድ የማሻሻል ንቅናቄን ዲላ ዩኒቨርሲቲ በመቀላቀል በአጼ ዳዊት ትምህርት ቤት የነበረውን ለአገልግሎት ምቹ ያልሆነ ህንፃ ከትምህርት ቤቱ በመረከብ እንደ አዲስ ገንብቶና ለተማሪዎች ምቹ እንዲሆን አድርጎ ማስረከቡን ገልጸው፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ መሰል ድጋፎችን አጠናክሮ እንደሚቀጥል አያይዘው ገልጸዋል።
ክብርት ወ/ሮ ጫልቱ ሳኒ፣ የኢፌዴሪ ከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የሰራው በጎ ስራ አድንቀው፤ ከአካባቢው አስተዳደር ጋር ተቀናጅተው ከዚህ በላይ በመትጋት ስታንዳርዱን የጠበቀ ትምህርት ቤትና ግቢውን አረንጓዴ ለማድረግ ጠንካራ ስራ እንዲሰራ አሳስበዋል።
አበባየሁ ታደሰ (ዶ/ር)፤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በምክትል ርዕሰ መስተዳደር መዓረግ የማሕበራዊ ዘርፍ ሰብሳቢና የክልሉ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ፣ በበኩላቸው ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከአካባቢው አስተዳደር ጋር በመተባበር የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና ለውጥ ለማምጣት ዘርፈ ብዙ ስራዎች እያከናወነ እንደሚገኝ አስታውቀው፤ በአንጋፋው አጼ ዳዊት ትምህርት ቤት ለአገልግሎት አመቺ ያልሆነ ህንፃ ተረክቦ እንደ አዲስ ገንብቶ በማስረከቡ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ኢንጂነር በፍቃዱ መኩሪያ፣ የዲላ ዩኒቨርስቲ ግንባታ ፕሮጀክት ዋና ስራ አስኪያጅ፤ ግንባታው እንዲካሄድ የዩኒቨርሲቲው ማኔጅመንት ከፈቀደ በኋላ የግንባታ ፕሮጀክቱን ዲዛይን በማውጣት ወደ ስራ ገብቶ በስድስት ወራት ስራውን እንዳጠናቀቀ በመግለጽ ህንፃው ለመማሪያ ክፍሎች እና ለቢሮ አገልግሎት የሚሰጥ ህንጻ በዘጠኝ ሚሊዮን ብር ወጪ እንዳስገነባ ገልጸው ለዚህ ህንጻ የመቀመጫ ወንበር በዲላ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ መምህራን አገልግሎት የማይሰጡ ብረቶች እና ከአገልግሎት ተመላሽ የሆኑ ፈርኒቸሮችን ተጠቅሞ በመስራት ለአገልግሎት ዝግጁ ማድረጋቸውን አሳውቀዋል።
ከርክክብ መርሐ ግብሩ በኋላ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የፌዴራል፣ የክልል፣ የዞንና የከተማ አስተዳደር አመራሮች የተዘጋጀላቸውን ሀገር በቀል ችግኝ በመትከል በትምህርት ቤቱ አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et