ዲ.ዩ፤ ሐምሌ 23/2016 (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ተጠሪ የሆኑ ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤቶች የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እና የ2017 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ ላይ ግምገማ መካሄዱ ተገልጿል።
አቶ መሳይ ፍቅ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ፤ ለፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ተጠሪ በሆኑ 13 ዳይሬክቶሬቶች በቀረበው የ2016 ዓ.ም የዕቅድ አፈፃፀም ግምገማ እንዲሁም የ2017 በጀት አመት ዕቅድ ዙሪያ እያንዳንዱ የስራ ክፍል በአፈፃፀሙ ያሳያቸው ጠንካራ ጎኖች እንዳሉ ጠቅሰው በተለይ ከዚህ በፊት በፕሬዝዳንቱ የተቀመጠውን አቅጣጫ ተቀብለው አብዛኛው የሥራ ክፍሎች እንደየስራ ክፍሉ ባህሪ፣ እሴት የሚጨምሩ ስራዎች መስራታቸውን መመልከታቸውን ተናግረዋል።
አቶ መሳይ አክለውም በተወሰነ ደረጃ የበጀት እጥረቶች፣ የአንዳንድ ግብዓት እጥረቶች እና ደራሽ ተቋማዊ ስራዎች ደግሞ በተወሰነ ደረጃ በሙሉ አቅማቸው እንዳይፈፅሙ ተግዳሮት የሆኑባቸው ስራ ክፍሎችም ተለይተው በ2017 ዕቅዳቸው ላይ የማካካሻ እና እንዲሁም ልዩ ዕቅድ ማዘጋጀት እንደሚገባቸው አስተያየቶች መሰጠታቸውን አንስተዋል።
እያንዳንዱ የሥራ ክፍል ባቀረበው አፈፃፀም ግምገማ ላይ በ2016 በጀት ዓመት የታዩ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ተለይተው የተነሱ ሲሆን፤ ጠንካራ ጎኖችን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባና በጉድለት የተነሱ ጉዳዮችን ለማሻሻል እነዚህ ሁኔታዎች በ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ የተቋሙን ነባራዊ ሁኔታ ባገናዘበ መልኩ በዕቅድ መካተታቸው ተገምግሞ ለአፈጻጸማቸው አቅጣጫ ተቀምጧል፡፡
ዲላ ዩኒቨርሲቲ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ለወቅታዊ መረጃዎች
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: pirdir@du.edu.et






