ዲ .ዩ፤ ሰኔ 25/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ጤና ሚኒስቴር ከዲላ ዩኒቨርሲቲ አጠቃላይ ሆስፒታል ጋር በመተባበር ያዘጋጀው ሀገር አቀፍ የSBFR አመታዊ አመፈጻጸም ግምገማ እና የእርስ በእርስ መማማሪያ መድረክ በዲላ ዩኒቨርሲቲ በመካሄድ ላይ ይገኛል።
በጉባኤው ላይ የተገኙ እንግዶችንና ተሳታፊዎችን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መልዕክት ያስተላለፍት ዝናቡ ወልዴ (ዶ/ር )፣ የጌዴኦ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ አባል፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በዲላ አጠቃላይ ሆስፒታል የነበረውን አፈጻጸም ለመገምገም በእንደዚህ አይነት ሁኔታ ሀገር አቀፍ መድረክ አዘጋጅቶ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላቶች ጋር ልምድ እንድንለዋወጥ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ይህን ስላመቻቸ በጌዴኦ ዞን አስተዳደር ስም ምስጋናዬን ላቀርብ እወዳለው ብለዋል።
በዚህ ከሰኔ 25 -26 /2016 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በሚቆየው አመታዊ ጉባኤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ሆስፒታል የጤና ስርዓት ማነቆዎችን መሰረት ያደረገ ሪፎርም ከማሻሻል አንጻር የሰራቸው ስራዎች በጤና ሚኒስቴር ኃላፊዎች እና በተሳታፊዎች ምልከታ ተካሂዶ ግብረ መልስ እንደሚሰጥበት ይጠበቃል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በጋራ ባዘጋጁት በዚህ አመታዊ ጉባኤ ላይ የተለያዩ ሆስፒታሎች የSBFR ትግበራ አመፈጻጸም እንደሚገመገም ተገልጿል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et



