Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

Top News

መጋቢት 05/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ም)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት አጋርነት ዳይሬክቶሬት በጌዴኦ ዞን ለሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች፣ በምዕራብ ጉጂ ዞን ለአባያ ወረዳ እና ለሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳ የንግድና ገበያ ልማት ባለሙያዎች በገበያ ጥናት መረጃ አሰባሰብ፣ ትንተናና ስርጭት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱ ታውቋል።
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የጌዴኦ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ ሰላማዊት ያሬድ፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በዞኑ የሚታዩ ክፍተቶች ላይ የስልጠና ድጋፍ እንዲያደርግልን ባቀረብነው ጥያቄ መሰረት ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠው የዛሬው ስልጠና በገበያ ጥናት ዘርፍ በመረጃ ማሰባሰብ፣ ትንተና እንዲሁም ስርጭት ዙሪያ ያለውን ክፍተት የሚሞላ ስልጠና እንደሚሆን ተናግረዋል።
ወ/ሮ ሰላማዊት አክለውም፤ ስልጣኞች ያለባቸውን ክፍተት በመለየት በምን በኩል ማሻሻል እንደሚጠበቅባቸው በመገንዘብ ስልጠናውን በትኩረት ተከታትለው ከዚህ በፊት የሚስተዋሉ ችግሮችን በማስወገድ የተሻለ ውጤት ሊያስመዘግቡ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት አጋርነት ዳይሬክቶሬት በአጫጭር ስልጠና ዘርፍ አስተባባሪ አቶ ብሩህ ተስፋሁን በበኩላቸው፤ በዚህ ዙር ለንግድና የገበያ ልማት ባለሙያዎች የተሰጠው ስልጠና በአሁኑ ሰዓት እየታየ ያለውን የገበያ ጥናት መረጃ አሰባሰብና ትንተና ላይ የሚስተዋሉ ክፍተቶችን ሊፈታ የሚችል መሆኑ ታምኖበት እንደተሰጠ ገልጸዋል።
ስልጠናው የዩኒቨርሲቲው የማናጅመንት ትምህርት ክፍል በተወጣጡ መምህራን የተሰጠ ሲሆን ስልጠናውን ከሰጡት አሰልጣኞች መካከል ያነጋገርናቸው መ/ር ብርሃኑ በቀለ፣ ስልጠናው በህብረተሰቡ እና በባለሙያዎች መካከል ያለውን የመረጃ ክፍተት እንደሚሞላ አንስተው፤ መረጃ ሀብት እንደመሆኑ መጠን በአግባቡ ተሰብስቦና ተተንትኖ ልንጠቀምበት ይገባል ሲሉ ገልጸዋል። ስልጠናውን የወሰዱ ሰልጣኞች የእውቀትና የክህሎት ሽግግር በማድረግ ባልደረቦቻቸውን በማሰልጠን በዘርፉ የተሻለ አሰራር መፍጠር ይገባቸዋልም ብለዋል።
የመዘጊያ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት አጋርነት ዳይሬክተር አቶ ተካልኝ ታደሰ፤ አርሶ አደሩ ምርት አምርቶ ወደ ገበያ በሚያመጣበት ወቅት ባነሰ ዋጋ ሸጦ ነጋዴ ደግሞ ለማህበረሰቡ ሲያደርስ የተጋነነ ዋጋ የሚሆነው በምን ምክንያት እንደሆነ በተሰጠው ስልጠና መሰረት የገበያ ጥናት መረጃ በመሰብሰብና በመተንተን ለህብረተሱ ትክክለኛውን መረጃ እንደምታደርሱ አምናለሁ ሲሉ ለሰልጣኞች ተናግረዋል።
ስልጠናውን ሲሳተፉ ያገኘናቸው ከጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ንግድና ገበያ ልማት ጽ/ቤት የመጡት ሰልጠጣኝ ወ/ሮ አትጠገብ ሲሳይ እንዲሁም ከሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳ የመጡት አቶ በረከተ ገሰሰ፤ ከስልጠናው ትልቅ ግንዛቤ እንዳገኙ በመግለጽ ዲላ ዩኒቨርሲቲ መሰል ስልጠናዎችን በማዘጋጀት ማህበረሰቡን እያገዘ በመሆኑ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

gtadmin