Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

“አድዋ ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ”
ዲዩ ጥር 24/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በዛሬው እለት “አድዋ ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ምክክር አካሂደዋል።
ታምራት በየነ (ዶ/ር)፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፕሬዝዳንቱ ተወካይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ዓድዋ የሰው ልጅ ሰው መሆኑን ያረጋገጠበት፣ ጥቁር ከነጭ ጋር እኩል መሆኑን ያተመበት፤ አሸናፊ የሚኮነው በሚኖረው ጠንካራ ስብዕና እና በሚያዘው ፍትሃዊ ዓላማ እንጂ በመሳሪያ ጋጋታ እንዳልሆነ ያመላከተ ክስተት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
ዶ/ር ታምራት አክለውም፤ የዓድዋ ድል አባቶቻችን በአንድነት መንፈስ ተመው ወራሪውን ቅኝ ገዥ ድል ያደረጉበት እና እኛ ልጆቻቸውም በዚህ የአባቶቻችን ተጋድሎ የምንኮራበት ነው ብለዋል፡፡
አያይዘውም ይህ ታሪክ የኢትዮጵያውያን ብቻ ሳይሆን የአፍሪካውያን እና የጥቁር ህዝቦች ታሪክም ጭምር እንደሆነ ገልጸው፤ የዓድዋ ድል ለፓን አፍሪካንዝም እንቅስቃሴ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረገ በርካታ ሀገራት ራሳችንን ማስከበር እንችላለን እንዲሉ ፈር የቀደደ ድል እንደሆነ ገልጸዋል፡፡
አቶ መሳይ ፍቅሩ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ በበኩላቸው ዲላ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ በአንድ ሀገር ውስጥ ያሉ ተቋማት ውጤታማ ሥራ መስራት የሚችሉት ጠንካራ ሀገር ሲመሰረት እንዲሁም ጠንካራ ሀገረ መንግስት ሲኖር ነው ብለዋል፡፡ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጠንካራ ሀገረ መንግስት እንዲመሰረት አስተዋፅኦ ሊያበረክቱ እንደሚገባ እና እነዚህ ተቋማት ሀሳቦች የሚፈልቁባቸው፤ ምርምሮች የሚካሄዱባቸው ከመሆኑ አኳያ ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ ዘመኑን የሚመጥኑ የተሻሉ ሀሳቦች የሚያመነጩባቸው ልዩ ልዩ መድረኮችን ማዘጋጀት እንደሚገባ ገልጸዋል።
አብዱ መሐመድ (ዶ/ር) በዲላ ዩኒቨርሲቲ የታሪክ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች መምህርና ተመራማሪ፤ የዓድዋ ድልና የአፍሪካ እድል በሚል ባቀረቡት የውይይት መነሻ ጽሁፍ የዓድዋ ድል እና ድሉ ለአፍሪካውያን ይዞት የመጣውን ነጻ የመሆን እድል በስፋት ዳሰዋል። ድሉ ለአፍሪካውያን ኩራትን ያቀዳጀ ለቀኝ ገዥዎች ውርደትን ያከናነበ ታሪካዊ ክስተት እንደሆነም ገልጸዋል።
ከዚህ በተጨማሪም በተለያዩ ዘመናት ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት የተሰራውን ስራ አብራርተዋል። የዓድዋ ድልን መድገም የሚቻለው ሰላምን በማስፈንና ጠንካራ ሀገረ መንግስት በመገንባት እንደሆነም ገልጸዋል። ለዚህም የአስተሳሰብ አብዮት (Mental Revolution) ማካሄድ እንደሚገባ ዶ/ር አብዱ አስረድተዋል።
ዶ/ር አብዱ በቀረቡት የመወያያ መነሻ ጽሑፉ ሃሳብና አስተያየቶች የቀረቡ ሲሆን የቀረበው ጽሑፍ ሀገር እንዴት መቀጠል እንደምትችልና እኛም ምን እንደሚጠበቅብን አቅጣጫ ያመላከተ አጠቃላይ የአመለካከት፣ የአስተሳሰብ እና የአሰራር ለውጥ እደሚያስፈልግ ግንዛቤ የተያዘበት ውይይት እንደነበር ተሳታፊዎች ገልጸዋል።
ከምክክር መድረኩ ተሳታፊ ምሁራን መካከል መ/ር ገመቹ ኦላኒ፤ የዓድዋ ድል በሀገራችን ታሪክ ውስጥ ትልቅ ቦታ የሚሰጠውና ዘር፣ ጾታ፣ አከባቢ ሳይለያቸው ኢትዮጵያውያን የተሳተፉበት ድል እንደሆነ ገልጸው የቀረበው የውይይት መነሻ ሀሳብ አድዋን ለሀገር ልማት፣ እድገትእና ጽናት መንዝረን መጠቀም እንደሚኖርብን ያመላከተ እንደሆነ አስረድተዋል።
ዶ/ር ያረጋል ሙሉ ሌላው የውይይቱ ተሳታፊ፤ የዓድዋ ድል ኢትዮጵያውያን ከጫፍ እስከ ጫፍ በነቂስ ወጥተው በሽዎች የሚቆጠሩ ኪሎሜትሮችንበእግራቸው ተጉዘው የጣሊያንን ቅኝ ገዥ ድባቅ በመምታት ነጭ በጥቁር እንደሚሸነፍና የሰው ልጅ ሁሉ እኩል እንደሆነ ያረጋገጡበት ድል እንደሆነ ገልጸዋል።
በምክክር መድረኩ የዩኒቨርስቲው የበላይ አመራሮች፣ መምህራን፣ ሰራተኞች፣ የሀይማኖት አባቶች፣ አባገዳዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ተማሪዎች ተሳትፈዋል።