Dilla University

News
Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Dilla University signed MOU with Nanjing University to work in partnership

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call for Application: Workshop on Direct Marketing atHSWT & HdbL – Germany

Call For Papers

Call For Papers

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ ሚያዝያ 22/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የአፍሪካ አገር በቀል ዛፎች ቀን የዲላ ዩኒቨርሲቲ የማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክቶሬት ከዕፅዋት ጥበቃ እና ኢኮ-ቱሪዝም ማዕከል ጋር በመተባበር “አገር በቀል ዛፎችን በትምህርት ቤቶች በመትከል እና በመንከባከብ ተፈጥሮን እንጠብቅ” በሚል መሪ ሀሳብ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ዕፅዋት ጥበቃ እና ኢኮ-ቱሪዝም ማዕከል ባዘጋጁት መርሃ ግብር ተከብሮ ውሏል።
ታሊሞስ ሴታ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የዕፅዋት ጥበቃና ኢኮ-ቱሪዝም ማዕከል ዳይሬክተር፤ የአፍሪካ አቀፍ ሀገር በቀል ዛፎች ቀን ዋና ዓላማው የብዘሃ ህይወት መመናመንን መከላከል መሆኑን አስረድተዋል።
ዶ/ር ታሊሞስ አክለውም፤ የእለቱ መርሃ ግብር አንዱ አካል የሆነው በቆፌ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ሀገር በቀል ችግኝ የመትከል መርሃግብር ሀገር ተረካቢ ተማሪዎችን በማሳተፍ ለቀጣይ ትውልድ አረንጓዴና ጤናማ ነገን ለማውረስ ያለመ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
አቶ ዮሐንስ ታደሰ፣ በጌዴኦ ዞን ደን፣ አካባቢ ጥበቃ እና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ በበኩላቸው፤ በተፈጥሮ ላይ የሚደርሱ ችግሮችን ለመቅረፍ ዛፎች ትልቅ ሚና እንዳላቸውና በአየር ንብረት ለውጥ አሳሳቢ በሆነበት በዚህ ወቅት ምላሽ ሊሰጥ የሚችል የአፈርና ውሃ ጥበቃና እንክብካቤ ስራ አስፈላጊ መሆኑን አንስተዋል።
በአየር ንብረት ለውጥና በሌሎች ተያያዥ ምክንያቶች የሙቀት መጠን መጨመር፣ ንፋስ የቀላቀለ ዝናብ፣ ጎርፍ ብሎም ድርቅ ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው፣ ለመጥፋት የተቃረቡና ለአደጋ የተጋለጡ ሀገር በቀልና ሌሎችን ዕፅዋቶች እንዳይጠፉ ለመታደግ መንከባከብ እንደሚያስፈልግ አስገንዝበዋል።
በግብርናና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ የሆርቲካልቸር ትምህርት ክፍል መምህር ምትኩ ሟነንዳ በበኩላቸው፤ ለመርሃ ግብሩ ታዳሚዎች ባቀረቡት ጽሑፍ ወቅታዊ የአየር ንብረት ለውጥና መንስዔውን ዳሰው ሀገር በቀል ዕፅዋቶችን በትምህርት ቤቶችም ጭምር በመትከል ከተፈጥሮ ጋር የተስማማ አኗኗርን መከተል እንደሚገባ አስረድተው፤ ዕፀዋትን ከመትከል ባለፈም ስለ ዕፅዋቶች ፋይዳ ግንዛቤ መፍጠርና የአከባቢ ጥበቃ ክበባትን ማጠናከር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
ፈጠነ ባሌሲ፣ በማሕበረሰብ አገልግሎትና አጋሪነት ዳይሬክቶሬት የሥልጠናና ማማከር ኦፊሰር በበኩላቸው፤ እየታየ ያለውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመቋቋም በዋናነት የሚያስፈልገው ሀገር በቀል ዕጽዋቶችን በመትከል እንደሆነና ይህንን በተመለከተ ግንዛቤ ማስጨበጥ አስፈላጊ መሆኑ ታምኖበት የተዘጋጀ መርሃግብር መሆኑን አስረድተዋል።
በመርሃግብሩ ከተሳተፉት መካከል በቆፌ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ12ኛ ክፍል ተማሪ መስከረም ከበደ፤ ዕፅዋት ለሰው ልጅ ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ እንዲሁም እንዴት መጠበቅ እንዳለባቸው ጥሩ ግንዛቤ ማግኘቷን ገልጻልናለች።
በመርሃ ግብሩ ማጠናቀቂያ ላይም የመርሃ ግብሩ ታዳሚዎች በቆፌ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሀገር በቀል ዛፎች ችግኝ ተከላ አከናውነዋል።
በፕሮግራሙ ላይ ከጌዴኦ ዞን የተለያዩ የቢሮ ኃላፊዎች፣ ከዲላ ከተማ አስተዳደር፣ ከከተማ ትምህርት ቤቶች የተጋበዙ መምህራን፣ ተማሪዎች እንዲሁም ከዩኒቨርሲቲ የተለያዩ ክፍሎች የተጋበዙ መምህራንና ሰራተኞች ተሳታፊ መሆናቸው ታውቋል፡፡
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et