Dilla University

News
Dilla University Hosts 14th Annual National Research Conference

Dilla University Hosts 14th Annual National Research Conference

Upcoming Event: 14th DU Annual National Research Conference

Upcoming Event: 14th DU Annual National Research Conference

Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፤ መጋቢት 12/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በመማር ማስተማር፣ በተልዕኮ ልየታ እና በዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ዙሪያ ከመምህራን ጋር ውይይት አካሂዷል።
ወንደሰን ገበየው (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ዲን በመድረኩ ባደረጉበት ንግግር፤ አጠቃላይ የትምህርት ስርዓቱን ሪፎርም ለማድረግ ያስችል ዘንድ በተዘጋጀው የትምህርት ፍኖተ ካርታ፣ የመማር ማስተማር ሂደት እና በዩኒቨርስቲ የመውጫ ፈተና ከመምህራን ጋር መወያየት አስፈላጊ በመሆኑ የተዘጋጀ ውይይት መሆኑን ጠቁመዋል።
ዶ/ር ወንደሰን አክለውም፤ የተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅና በስሩ የሚገኙ ትምህርት ክፍሎች ተግባራዊ ትምህርት እና የመምህራን ትምህርት በዋናነት ሲሰራበት እንደቆየና በአዲሱ የትምህርት ፍኖተ ካርታም በተሰጠው ተልዕኮና ዓላማ ለማሳካት ከመምህራን ጋር ሰፊ ውይይትና የምክክር መደረጉን አስገንዝበዋል ።
መምህር ማቴዎስ ሆሲሳ፣ በተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ተወካይ የአካዳሚክ ምክትል ዲን በበኩላቸው፤ በመድረኩ በመማር ማስተማር የተከናወኑና እየተከናወኑ ያሉ ስራዎችን እንዲሁም በ2015 ዓ.ም የተሰጠው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ውጤት ሪፖርትና በ2016 ዓ.ም የሚሰጠው የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና የስራ ዕቅድ አቅርበው በመድረኩ ተሳታፊዎች ውይይት ተካሂዶባቸዋል።
በ2015 ዓ.ም ኮሌጁ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና ከወሰዱት ተማሪዎች 81.37 በመቶ ተማሪዎችን በማሳለፍ በዩኒቨርሲቲው 3ኛ ደረጃ መያዙ ይታወቃል። ለተመዘገበው ውጤት አስተዋጽኦ ላበረከቱ ትምህርት ክፍሎች እና ባለድርሻ አካላት የእውቅና ምስክር ወረቀት የመስጠት ስነ ስርዓት ተካሂዷል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et