Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

Top News

ዲ.ዩ፤ ሐምሌ 5/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፤ በዲላ ዩኒቨርሲቲ ከሐምሌ 3 እስከ 5 /2016 ዓ.ም በወረቀት እና በበይነ መረብ ሲሰጥ የቆየው የመጀመሪያ ዙር የማህበራዊ ሳይንስ የ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ዛሬ ተጠናቋል፡፡
በዲላ ዩኒቨርሲቲ ከሐምሌ 3 እስከ 5 በመጀመሪያ ዙር ሲሰጥ የቆየው የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና መጠናቀቁን አስመልክቶ፤ ማቲዎስ ሀብቴ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክተርና የአካዳሚክ ጉዳዮች ም/ፕሬዝዳንት ተወካይ እንዲሁም ተመስገን እንግዳ (ዶ/ር)፣ የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ በጋራ መገለጫ ሰጥተዋል፡፡
ዶ/ር ማቲዎስ ሀብቴ በመግለጫቸው፤ ላላፉት 3 ቀናት በኦዳያኣ እና በነባሩ ግቢ የፈተና ጣቢያዎች በወረቀት እና በበይነ መረብ ሲሰጥ የቆየው የማህበራዊ ሳይንስ የ12ኛ ክፍል ፈተና እንደ ዩኒቨርሲቲ ከ10,000 በላይ ተማሪዎችን በማስፈተን ያለምንም የፀጥታ ችግር በሰላም መጠናቀቁን ገልጸዋል።
በዚህም ከዲላ ከተማ እና ከአጎራባች ከተሞች የመጡ ተማሪዎች ዛሬውኑ መውጣት የጀመሩ ሲሆን ነገ ቅዳሜ ደግሞ ራቅ ካለ ቦታ የመጡ ተማሪዎች ሽኝት ተደርጎላቸው ከእሁድ ጀምሮ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቅበላ እንደሚደረግ ዶ/ር ማቲዎስ አያይዘው ተናግረዋል።
ዶ/ር ማቲዎስ አክለውም፤ በዚህ ሳምንት ለማህበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች የተደረጉ ዝግጅቶች ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎችም እንደሚደረጉና ቀጣይ የፈተና መርሀ ግብርንም በስኬት እንደሚያጠናቅቁ ገልጸው፤ በዚህም የማህበራዊ ሳይንስ ፈተና በስኬት እንዲጠናቀቅ የራሳቸውን ሚና ለተወጡ ከፀጥታ አካላት ጀምሮ፣ ለትምህርት ሚኒስቴር ባለሙያዎች፣ ለጉድኝት ኃላፊዎች፣ ለቺፎች፣ ለሱፐርቫይዘሮች፣ ለፈታኞችና ለሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ተመስገን እንግዳ (ዶ/ር ) የፕሬዝዳንቱ ልዩ አማካሪ በበኩላቸው፤ በዩኒቨርሲቲው ከሐምሌ 3 ጀምሮ በሁለቱም ግቢዎች ላይ ሲሰጥ የቆየው የማህበራዊ ሳይንስ የፈተና ሂደት ያለምንም ችግር ፍጹም ሰላማዊ ሆኖ በስኬት መጠናቀቁን ተናግረዋል።
ለዚህም ደግሞ የፈተና ሂደቱ ከፈተና ደንብ ጥሰትና ኩረጃ ፍጹም የጸዳ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የፀጥታ እና የደህንነት ግብረ ኃይሉ ፀሐይ እና ዝናብ ሳይበግራቸው በዩኒቨርሲቲው አካባቢ እና በውስጥ ያለውን የተማሪዎች ደህንነት በመጠበቅ የፈተና ስርዓቱ በተገቢው መንገድ እንዲሄድ ከፍተሻ ጀምሮ ትልቅ ሚና የተጫወቱ በመሆናቸው በዩኒቨርሲቲው ስም ላመሰግናቸው እወዳለው ሲሉ ዶ/ር ተመስገን ተናግረዋል።
በመጀመሪያው ዙር በማህበራዊ ሳይንስ ዘርፍ ፈተናቸውን አጠናቀው ሲወጡ ያነጋገረናቸው ተፈታኞች ተማሪ አብዱል ፈታ ሀሰን እና ተማሪ አህመድ አደም ኢብራሂም በበኩላቸው፤ ፈተናው በሰላም መጠናቀቁ እንዳስደሰታቸው ገልጸው፤ በዩኒቨርሲቲው ከመጀመሪያ ቀን ጀምሮ ለተደረገላቸው መልካም አቀባበል እና ለነበራቸው ቆይታ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
ከዲላ ከተማ እና አቅራቢያ ከተሞች የመጡ ተፈታኝ ተማሪዎች ዛሬ ማታ የተሸኙ ሲሆን ሌሎች ከሱማሌ ክልል እና ከኦሮሚያ ሻሸመኔ አካባቢ የመጡ ተማሪዎች በነገው እለት እንደሚሸኙ ተገልጿል።
ከዩኒቨርሲቲ በነገው እለት ለሚመለሱ ፈታኝ መምህራን እና ለተፈታኝ ተማሪዎች መልካም ጉዞ እንዲሆንላቸው እንመኛለን።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et

gtadmin

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *