ዲ.ዩ ግንቦት 19/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ) በዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምር ስነ ምግባር ህትመትና ስርጭት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ከጆንሰን የጠፈር ምርምር ማዕከል የመጡ ከፍተኛ ተመራማሪ ‘የጠፈር ምርምር ተግዳሮቶች እና ጥቅሞች’ /Human space Science: Challenges and Opportunities) በሚል ሐሳብ ፐብሊክ ሌክቸር ተሰጥቷል።
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምርምር ስነ ምግባር፣ ህትመትና ስርጭት ዳይሬክተር፣ ምስጋኑ ለገሰ (ዶ/ር) ባደረጉት ንግግር፤ ለዩኒቨርሲቲያችን ብሎም ለሀገራችን የዚህ አይነቱ ርዕሰ ጉዳይ ላይ የሚደረጉ ውይይቶች አስፈላጊ መሆናቸውን ገልጸው፤ የሚደረገው የልምድ ልውውጥ ከሌሎች የትምህርት ተቋማት ጋር ያለንን ግንኙነት ከማጠናከር በዘለለ በዘርፉ ለምናደርገው መማር ማስተማር፣ ለተማሪዎችና ተመራማሪዎች መነሳሳትን የሚፈጥር ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ዲስኩሩን ያቀረቡት ዶክተር ጥላዬ ታደሰ፣ በአሜሪካ የህዋ ምርምር ጣቢያ የጆንሰን የጠፈር ምርምር ማዕከል ከፍተኛ ተመራማሪ በበኩላቸው፤ በህዋ ሳይንስ የበለጸጉ አገራት የሚያደርጉት ምርምር ምድርን በብዙ ዘርፍ እንዳሻሻለ ገልጸው፤ የህዋ ሳይንስን መረዳት መቻል ያለውን ዘርፈ ብዙ ጠቀሜታ አስረድተዋል።
ዶክተር ጥላዬ አክለውም፤ የሰውን ልጅ ጤንነት፣ ትራንስፖርት፣ የህብረተሰብ ደህንነት የመሳሰሉ ጥናቶች ከህዋ ሳይንስ የተገኙ መሆናቸውንም አንስተዋል።
በወቅቱ ውይይቱን ሲሳተፉ ያገኘናቸው፣ አስናቀ ሙሉዬ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የመረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር፤ የተሰጠው ፐብሊክ ሌክቸር ጠቀሜታው የጎላና ትልቅ እድል መሆኑን ገልጸው፤ በተለይ ደግሞ በዘርፉ እውቀትን ባካበተ የአገር ልጅ መሰጠቱ እንዳስደሰታቸው ገልጸውልናል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et






