ዲዩ. ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ) የዲላ ዩኒቨርሲቲ ልኡክ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት ናዳ በደረሰበት ስፍራ ተገኝቶ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ቤተሰብ አጽናንቶ የተለያዩ ግብዓቶችን አስረክቧል።
የልኡክ ቡድኑን መርተው በስፍራው የተገኙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ ተመስገን እንግዳ (ዶ/ር)፤ ባደረጉት ንግግር የዩኒቨርሲቲው ማኔጂመንት ባደረገው ውይይት በተጎጂ ወገኖች ላይ የደረሰውን ከባድ ሐዘን ለመጋራትና ለማጽናናት ብሎም ድጋፎችን ለማድረግ ልኡክ ቡድኑ በስፍራው እንደተገኘ ገልጸዋል።
ዶ/ር ተመስገን አክለውም፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ መሰል የዜጎችን ርብርብ የሚፈልጉ ጉዳዮች ሲኖሩ በግንባር ቀደምነት ተሰልፎ ድጋፎችን በማድረግ እንደሚታወቅና የዛሬው ድጋፍም አንዱ ማሳያ እንደሆነ ገልጸዋል። ጉዳቱ የደረሰበት አከባቢ ያሉ ሰዎች አሰፋፈር ከአከባቢው መልክአ ምድር አቀማመጥ ጋር ተደማምሮ ለጉዳቱ መባባስ ምክንያት በመሆኑ የህብረተሰቡን አሰፋፈር ማጥናት የሚያስፈልግ በመሆኑ በአከባቢው ስነምዳር ላይ ጥናት ማድረግ እንደሚገባ ገልጸው ጉዳቱ ለደረሰባቸው ቤተሰቦች መጽናናትን ተመኝተዋል።
አቶ መሳይ ፍቅሩ፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ በዛሬው እለት የተደረገው ድጋፍ ለተጎጂ ወገኖች የእለት ምግብ የሚሆኑ ሞኮሮኒ እና ሩዝን ጨምሮ ለመኝታ አገልግሎት የሚውሉ ፍራሾችን እንደሚያካትት ገልጸው ወደፊትም በጥናት ላይ የተመሰረተ ድጋፍ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲው ዝግጁ መሆኑን አስገንዝበዋል።
በተያያዘ ዜና የዩኒቨርሲቲው ልኡክ ቡድኑ አባላት በደረሰው ጉዳት ማህበረሰቡን ለማጽናናት በስፍራው ከተገኙት ጠቅላይ ሚንስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ ጋር በመሆን ህይወታቸውን ላጡ ዜጎች መታሰቢያ የሚሆን ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ለወቅታዊ መረጃዎች
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: pirdir@du.edu.et