Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዲ.ዩ፦ ሐምሌ 2/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ በዘንድሮ የትምህርት ዘመን በመጀመሪያ ዙር (ማህበራዊ ሳይንስ ) የሚወስዱ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎች ተጠቃለው መግባታቸው ተገልጿል።
በዩኒቨርሲቲው ከሐምሌ 3 -12 በሚቆየው የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ተጠቃለው መግባታቸውን አስመልክቶ፤ ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት እና ደረጀ አንዱዓለም (ዶ/ር)፣ የአስ/ልማ/ምክትል ፕሬዝዳንት መግለጫ ሰጥተዋል፡፡
ዶ/ር ችሮታው አየለ በመግለጫቸው፤ እንደ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ.ም ከ17 ሺህ በላይ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች በተፈጥሮ እና በማህበራዊ ሳይንስ ፈተና እንደሚፈተኑ ገልጸው በዚህም የመጀመሪያው ዙር የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከአርብ ጀምሮ በመግባት በትላንትናው ዕለት ሙሉ በሙሉ ተጠናቀው መግባታቸውን ገልጸዋል።
በዚህም ለተማሪዎች የሚያስፈልገው የተማሪዎች የመኝታ እና የምግብ አገልግሎት የተሰጠ እንደሆነ ተናግረው ፤ ከዛ ባሻገር በዛሬው ዕለት ለፈተና አስፈጻሚዎች የእንኳን ደህና መጣችሁ እና የገለጻ ፕሮግራም እንደሚከናወን ዶ/ር ችሮታው አያይዘው ተናግረዋል።
ዶ/ር ችሮታው አክለውም፤ ከሰዓት በኃላ በሁለቱም ግቢዎች ማለትም በነባሩ ግቢ እና በኦዳያኣ ግቢዎች ላይ የተማሪዎች ገለጻ በዝርዝር እንደሚሰጥ ገልጸው ፤ ተማሪዎች በቆይታቸው ፈተናቸውን በተመቻቸ ሁኔታ ወስደው ወደየመጡበት እንዲመለሱ በተቋሙ 24 ሰዓት እንደሚሰራ በመግለጽ ለተፈታኞቹ እንኳን ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ በሰላም መጣችሁ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ደረጀ አንዱዓለም (ዶ/ር) ፣ የአስ/ል/ምክትል ፕሬዝዳንት በበኩላቸው፤ በዩኒቨርሲቲው ዘንድሮ የ12ኛ ክፍል ብሄራዊ ፈተናን በተመለከተ ቀደም ብሎ በፕሬዝዳንቱ አቢይ እና ንዑሳን ግብረ ኃይሎች ተቋቁመው ሰፊ ስራዎች ሲሰሩ እንደነበር ገልጸው፤ በዚህም ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲው መግባት ከጀመሩበት ቀን አንስቶ ማደሪያቸውን ዝግጁ በማድረግ እና በመቀበል በትላንትናው እለት ሙሉ ለሙሉ ተማሪዎች ተጠቃለው በመግባት ለፈተናው መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል።
ዶ/ር ደረጃ አክለውም፤ ከተማሪዎች አገልግሎት ረገድም በምግብ አቅርቦት ፣ በመኝታ፣ በህክምና እንዲሁም በሌሎች መስኮች በበቂ ሁኔታ ዝግጅት መደረጉን በመግለጽ ለተማሪዎች የግቢ ቆይታቸው መልካም እንዲሆን ተመኝተዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መርሃ ግብር መሰረት በዩኒቨርሲቲው ከሐምሌ 3-11 /2016 ዓ.ም በሚካሄደው አገር አቀፍ ብሔራዊ ፈተና ከ17,500 በላይ ተማሪዎች ብሄራዊ ፈተናውን እንደሚወስዱ ታውቋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት


Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et