Dilla University

News
Training Provided on Research Ethics and Integrity

Training Provided on Research Ethics and Integrity

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎች ምረቃ ስነ-ስርዓት

Call For Papers

Call For Papers

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University became the first Ethiopian Public university Certified on a Good Financial Grant Practice (GFGP)

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Dilla University Held Its Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Upcoming Event: Dilla University’s Annual Research Validation Workshop

Call for paper

Call for paper

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

6th Science Week Symposium: Robotics and Artificial Intelligence for Societal Transformation

Call For Research Propossals

Call For Research Propossals

Upcoming Event

Upcoming Event

Green University, Sustainable Future

Top News

ዶ/ር ታምራት አያይዘውም፤ ሽግግሩን ወደ ተግባር ለመቀየር ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የሚያስፈልገውን አደረጃጀት በማቋቋምና በቂ የፋይናንስና ግብዓቶችን በማሟላት ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካለት ጋር በቅንጅት በመስራት ርብርብ እንደሚደረግ አስገንዝበዋል።

ታምራት በየነ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትና የፕሬዚዳንቱ ተወካይ፤ በስልጠናው የመዝጊያ መርሐ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር፤ ሁሉንም የኮሌጅ ዲኖች፣ ምክትል ዲኖች እና በአካዳሚክ ዘርፍ ያሉ ዳይሬክተሮችን ያካተተ ለስርዓተ ትምህርት ቀረፃና ክለሳ ወሳኝ ሚና ያላቸውን ምሁራን ያሳተፈ ስልጠና መሰጠቱን ጠቅሰው፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ (UAS) እንደመሆኑ መጠን ትኩረት በተደረገባቸው በግብርና፣ በተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ በጤናና የመምህራን ትምህርት ላይ ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት የተለያዩ ስልጠናዎች ሲሰጡ ቆይተው አሁን ወደ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃና ክለሳ ለመሸጋገር ስልጠና የወሰዱት አመራሮች ጉልህ ሚና እንደሚይዙ ገልጸዋል።

ጌታነህ ሞሱ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የልየታና ትኩረት መስክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ ስልጠናው በዘርፉ በቂ እውቀትና ሰፊ ልምድ ያካበቱ እንዲሁም በተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ በአገር አቀፍ ደረጃ የስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ተሳትፎ እያደረጉ ባሉት ይልማ ገዙ (ዶ/ር) እና ቸርነት አይተንፍሱ (ዶ/ር) ለተከታታይ ሁለት ቀናት መሰጠቱን ገልጸው፤ አመራሩ በስልጠናው ያገኘውን እውቀትና ግንዛቤ የተጀመረውን ለውጥ ተግባራዊ ለማድረግ የራሱን ድርሻ ለመወጣትና በስሩ ያሉ መምህራን፣ የትምህርት ክፍል ሀላፊዎችና ባለሙያዎች በማስተባበርና የጋራ ግንዛቤ በመፍጠር ለስራው መሳካት ወሳኝ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

ስልጠናውን ከሰጡት መካከ ዶ/ር ቸርነት አይተንፍሱ፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የትምህርትና ሰነ ባህሪ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ እንደገለፁት፤ ስልጠናው ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተሰጠውን የተልዕኮ ልየታና የመስክ ትኩረት ማዕከል ያደረገ የስርዓተ ትምህርት ቀረፃና ክለሳ የአካዳሚክ አመራሩ ግልጽና ወጥ የሆነ ግንዛቤ እንዲይዝ የተዘጋጀ መሆኑን አውስተው በስልጠናው በስርዓተ ትምህርት ጽንሰ ሐሳብ፣ በተግባራዊ ዩኒቨርሲቲዎች ተሞክሮ፣ የተግባራዊ ዩኒቨርሲቲዎች ስርዓተ ትምህርት ማዕቀፎችና ዙሪያና ሌሎች ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮችን ያካተተ ንቁ ተሳትፎ የነበረው ስልጠና እንደነበር ተናግረዋል።

ስልጠናውን ከወሰዱ መካከል መስፍን ደምሴ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ፕሮግራም ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር እና ደረጀ አየለ፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የቅድመ እና ድህረ ምረቃ ፕሮግራም ኦፊሰር በሰጡን አስተያየት፤ በተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ሽግግር ላይ የነበሩ ያልጠሩ ሀሳቦች የጋራ ግንዛቤ የተገኘበት፣ በቀጣይ ለሚካሄደው የስርዓተ ትምህርት ቀረፃና ክለሳ ወሳኝ የሚባሉ ሀሳቦች የተነሱበት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እንደነበረ አንስተዋል።

ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram:https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et