ዲ.ዩ፤ ግንቦት 21/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ) በዲላ የኢንዱስትሪ ግንኙነትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክቶሬት ጽ/ቤት ከ ጂ አይ ዜድ (GIZ) ጋር በመተባበር በአገር አቀፍ ደረጃ ለሚደረገው የAGRO – BUISNESS – IDEA – COMPETITION ውድድር ላይ ለሚሳተፉ ተወዳዳሪዎች ለ5 ቀናት የሚቆይ የ boot Camp ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።
በስልጠናው በዩኒቨርሲቲው ከ 2ኛ እስከ 4ኛ ዓመት በተለያዩ ትምህርት ክፍሎች የሚገኙ የአግሮ ቢዝነስ ሃሳብ ያላቸው ከ50 በላይ ሰልጣኞች ስልጠናውን እየተከታተሉ ይገኛል ።
በዚህ ስልጠና ተሳታፊ የሆኑ ሰልጣኞ ይህን የአምስት ቀናት የboot camp ስልጠና ከአጠናቀቁ በኃላ በስልጠናው የተመረጡ አምስት ፕሮጀክቶች እና 25 (ሀያ አምስት) ተወዳዳሪዎች ከሁለት ወራት የኢንኩቤሽን ጊዜ ቆይታ በኃላ በአገር አቀፍ ደረጃ በሚካሄደው የAGRO – BUISNESS – IDEA – COMPETITION 2024 ውድድር ላይ የሚቀርቡ መሆናቸውን በዪኒቨርሲቲው የኢንዱስትሪ ግንኙነትና ቴክኖሎጂ ሽግግር ዳይሬክተር አዲሱ ፍሪንጆ (ዶ/ር ) ገልጸዋል።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ፤
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://www.t.me
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et