ዲ.ዩ፤ ሐምሌ 19/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ም)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የልየታና ትኩረት መስክ ዳይሬክቶሬት ከፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ጋር በመተባበር በተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ (University of Applied Science) ስትራቴጂክ ማኔጅመንት ዙሪያ ለዩኒቨርሲቲው አመራሮች ላለፉት አራት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል።
ታምራት በየነ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዚዳንትና የፕሬዚዳንቱ ተወካይ፤ በስልጠናው መዝጊያ መርሐ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፤ ላለፉት አራት ቀናት በተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስትራቴጂክ ማኔጅመንት ዙሪያ ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በዛሬው እለት መጠናቀቁን ገልጸው ፤ ይህ ስልጠና በዋናነት ዲላ ዩኒቨርሲቲ አፕላይድ ዩኒቨርሲቲ እንደመሆኑ ለካውንስል አባላቱ አፕላይድ ዩኒቨርሲቲን ለመምራት ምን ምን ነገሮች ያስፈልጋሉ እንዲሁም ምን ምን ስራዎችን መስራት ይጠበቃል በሚሉትን ጉዳዮች ላይ መረጃ በመስጠት በልየታና ትኩረት መስክ ዙሪያ ግንዛቤያቸውን ወደ አንድ ለማምጣት በማሰብ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን አስረድተዋል።
ይህ ስልጠና ከዚህ ቀደምም ከትምህርት ሚኒስቴር እና ከጂ አይ ዜድ (GIz) ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር ለዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ መምህራን እና የአስተዳደር ሰራተኞች በአፕላይድ ዩኒቨርሲቲ ሽግግር እና አስተዳደር ዙሪያ በሁለት ዙር መሰጠት መቻሉን ዶ/ር ታምራት አያይዘው ተናግረዋል።
ዶ/ር ታምራት አክለውም፤ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደም በሚያስተምራቸው እና በሚያስመርቃቸው ተማሪዎች በትምህርት ጥራት ላይ አንቱታን ያተረፈ ትልቅ ተቋም እንደመሆኑ በቀጣይም ይሄንኑ መልካም ስም በተግባር ተኮር ትምህርቱ ላይም አስጠብቆ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
ከዚህ ጋር ተያይዞ ፤ ስልጠናው ክፍሎች እንዴት አብረው ተሰናስነው መስራት እንዳለባቸው ትልቅ ግንዛቤ ያስጨበጠ እንደመሆኑ እያንዳንዱ መምህር፣ ሰራተኛ እና የጽ/ቤት ኃላፊ ጭምር በዚህ ለውጥ ራሱን አቀናጅቶ ለመምራት ከወዲሁ ተገቢውን ቅድመ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅበት አስገንዝበዋል።
ጌታነህ ሞሱ (ዶ/ር)፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የልየታና ትኩረት መስክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ ከሐምሌ 16 ጀምሮ ለካውንስል አባላቱ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና በስኬት መጠናቀዉን ገልጸው፤ ለዚህም መሳካት በተለይ የከፈተኛ አመራሩ፣አሰልጣኞች፣ ሎጂስቲክ ኮሜቴ አባላት ሚና ከፍተኛ እንደነበር በመግለጽ ለስልጠናው መሳካት ድጋፍ ላደረጉ ሁሉ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።
ስልጠናውን ከሰጡት መካከል በዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ኮሌጅ ዲን መ/ር ታሪኩ ሌራቶ በበኩላቸው፣ የስልጠናው ዋና ዓላማ ዩኒቨርሲቲው በተሰጠው ልየታ መሰረት ወደ ስራ ለመግባት ሁሉም የዩኒቨርሲቲው አመራር አንድ ወጥ ሃሳብ እንዲኖራቸው ታሳቢ ተደረጎ የተሰጠ ስልጠና እንደሆነ ተናግረዋል።
ሰልጣኝ አመራሮች በስልጠናው ማጠናቀቂያ በይርጋለም አግሮ ኢንዲስትሪ ፓርክ በመገኘት የኢንዱስትሪ ትስስርን ለማጠናከር እና ስራዎችን በተግባር ለመመልከት የሚያስችል ጉብኝት ማደረጋቸው ከአዘጋጆቹ ተገልጿል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ለወቅታዊ መረጃዎች
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: pirdir@du.edu.et











