ዲ.ዩ፤ ሐምሌ 16/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ም)፦ በተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ (Applied Science University) ስትራቴጂክ ማኔጅመንት ዙሪያ ለዩኒቨርሲቲው አመራሮች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።
ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት በስልጠናው ላይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ ስልጠናው ለዩኒቨርሲቲው አስተዳደር ካውንስል አባላት በሙሉ የሚሰጥና የዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት የራሳቸውን አስተዋፅኦ ሊያበረክቱበት የሚገባ አስፈላጊ ስልጠና መሆኑን ጠቁመው፤ በአገራችን የትምህርት ስልጠና ፍኖተ ካርታ ዙሪያ ጥናት ተካሂዶ ዩኒቨርሲቲዎች በተልዕኮ ተለይተውና የትኩረት አቅጣጫ ተቀምጦላቸው በዚህ መሠረት ዲላ ዩኒቨርሲቲ ተግባራዊ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ (UAS) በመሆኑ ትኩረት በተደረገባቸው በግብርና፣ ተፈጥሮ ሀብት ጥበቃ፣ በጤናና በመምህራን ትምህርት በስፋት ትኩረት በማድረግ ዩኒቨርሲቲው ለሚሰራው ስራ ስልጠናው አሰፈላጊ በመሆኑ ሁሉም የአስተዳደር ካውንስል አባላት ንቁ ተሳትፎ በማድረግ ውጤታማ ስልጠና እንዲሆን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
አብዱ ሐሰን (ዶ/ር)፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የልየታና ትኩረት መስክ ዳይሬክቶሬት ምክትል ዳይሬክተር፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ታሪክ፣ አሁን ያለው ቁመናና ለቀጣይ ያለውን እቅድ፣ የተልዕኮ የልየታና የትኩረት አቅጣጫ ምንነት ፋይዳ በተመለከተ የመነሻ ፅሑፍ አቅርበዋል።
ጌታነህ ሞሱ (ዶ/ር)፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የልየታና ትኩረት መስክ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር በበኩላቸው፤ የተግባር ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ትራቴጂክ፣ ዓላማዎች እና ምክንያቶች፣ ተልእኮዎች፣ የመመሪያ መርሆዎች እንዲሁም የተግባር ዩኒቨርሲቲ ባህሪያት ዙሪያ ገለጻ ሰጥተዋል።
ስልጠናው ስትራቴጅካዊ አስተዳደር፣ የተግባር ተኮር ማስተማር ሂደቶች፣ የኢንዱስትሪ ትስስር፣ የሥራ ፈጠራና የውጭ ንግድ፣ ሥራ ፈጣሪነት፣ ምርምር፣ የቴክኖሎጂና የዕውቀት ሽግግር፣ የማህበረሰብ ተሳትፎና አጋርነት ወዘተ በሚሉ ጉዳዮች ዙሪያ ለቀጣይ አራት ቀናት እንደሚሰጥ ተገልጿል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ለወቅታዊ መረጃዎች
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: pirdir@du.edu.et






