Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
Call For Papers

Call For Papers

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

Join us for a colloquium on an important topic that intersects cultural heritage and Development

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

በዲላ ዩኒቨርሲቲ የሥነ ጽሑፍ ዝግጅት ተካሄደ

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

የሰራተኞችን ድልድል እየሰራ ያለው ኮሚቴ ስራ ምልከታ ተደረገ

#Upcoming_Event

#Upcoming_Event

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

በአፕላይድ ሳይንስ ዩኒቨርሲቲ ስርዓተ ትምህርት ቀረፃ ዙርያ ስልጠና ተሰጠ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለአቅመ ደካማና ለአካል ጉዳተኛ ቤተሰብ ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ አደረገ

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

አዲስ ለተሾሙት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት አቀባበል ተደረገላቸው

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

ዶ/ር ኤልያስ አለሙ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ጌዴኦ ዞን ዲላ ከተማ ገቡ

Top News

ዲ.ዩ፤ የካቲት 02/2016 ዓ.ም. (ህ.ዓ.ግ)፦ “ሆፕ ወክስ” (HOPE WALKS) በጎ አድራጎት ድርጅት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤና እና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል በመገኘት እግራቸው ቆልማማ በሆነ ታካሚዎች ዙሪያ ከጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ ለተወጣጡ 100 ለሚሆኑ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ስልጠና የሰጠ ሲሆን በሆስፒታሉ ቆልማማ እግር ላላቸው ታካሚ ህፃናት የህክምና አገልግሎት ድጋፍ አድርጓል፡፡
አቶ ትዝአለኝ ተስፋዬ፣ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤና እና ሕክምና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈፃሚ እንደገለፁት፤ ከቆልማማ እግር ጋር አብረው የሚወለዱ ህጻናት ችግር በተለምዶ በህክምና የማይስተካከል የሚመስል ትኩረት ሳይሰጠው አብሮ ያድግና ይህ ችግር ያለባቸው ሰዎች ከህብረተሰቡ የሚገለሉበት ሁኔታ እንደነበር ተናግረዋል፡፡
ነገር ግን ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ ከ “ሆፕ ወክስ” (HOPE WALKS) ጋር በጋራ በመሆን በአጥንት ህክምና ስር በዋነኛነት የቆልማማ እግር ክትትል የሚያደርግ ክሊኒክ ተከፍቶ በርካታ ህፃናትን ማከም እንደተጀመረ ገልጸው፤ በዚህም በርካታ እናቶች ልጆቻቸው ተሽሏቸው ቀጥ ብለው መሄድ እንዲችሉ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ገልጸዋል።
ወ/ሮ መዓዛ ካሳ፣ በጤና ሚኒስቴር ሜዲካል አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ የስፔሻሊቲ እና ሪሀብ ዴስክ የአፈጣጠር ችግር አስተባባሪ በበኩላቸው፤ በጤና ሚኒስቴር በሜዲካል አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ ስፔሻሊቲና ሪሀብ ዴስክ ውስጥ ከተያዙት ዕቅድ ውስጥ አንዱ የአፈጣጠር ችግርን ህክምና አሰጣጥ ላይ እንደመሆኑ መጠን በዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል 100 ለሚሆኑ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎችን የቆልማማ እግር ህክምና አገልግሎት የግማሽ ቀን ስልጠና ለመስጠት እና ለታካሚ ህፃናት የህክምና አገልግሎት ድጋፍ ለማድረግ የታሰበ መሆኑን ገልጸዋል።
ወ/ሮ መዓዛ አክለው፤ እነዚህ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ከህብረተሰቡ ተደራሽነት ያላቸው በመሆናቸው ህክምናውን ቀድሞ ከተለየ ከ2 ዓመት በታች ከሆነ የህክምና አገልግሎት በቀላል የመስተካከል ሁኔታ እንዳለ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መሰጠቱን ገልጸው፤ ይህንን ስራ ሲሰሩ HOPE WALKS በቆልማማ እግር ህክምና ላይ በጣም ትልቅ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ የሚገኝ በጎ አድራጎት ድርጅት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
ዶ/ር ብርሃኑ አያና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የአጥንት ህክምና ትምህርት ክፍል ውስጥ የህፃናት አጥንት ህክምና ኃላፊ እና HOPE WALKS ሜዲካል ዳይሬክተር፤ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች በገጠር አካባቢ ከህክምናው ጋር በተያዘ ስለሚሰሩ የቆልማማ እግር ልየታና የታካሚ ቅብብሎሽ ከጤና እና ከሆስፒታሉ ጋር ህክምናውን እንዲያገኙ የሚያደርግ ስልጠና እንደሆነ ገልፀው፤ ባለሙያዎች ከሰለጠኑ በኋላ የቆልማማ እግር ያለባቸውን በየአካባቢው ተደብቀው ያሉትን ህፃናት ህክምና መስጠት እንዲችሉ አሳስበዋል።
ዶ/ር አሸናፊ ነጋ፣ የአጥንትና መገጣጠሚያ ቀዶ ጥገና ስፔሻሊስት እንደገለፁት፤ በአለም ደረጃ በየቀኑ 500 የሚሆኑ ህፃናት ከዚህ ችግር ጋር እንደሚወልዱ እና ህክምናው 90 በመቶ በላይ ውጤታማ እንደሆነ አስረድተዋል።
ስልናውን ከወሰዱ ባለሙያዎች መካከል በዲላ ዙሪያ ወረዳ ሲሶታ ጤና ጣቢያ ዳይሬክተር አቶ ቢኒያም ጅግሶ፤ ልጆች ሳይሸማቀቁ ትምህርታቸውን እንዲማሩ ልጆች ጋር በነፃናት እንዲጫወቱ እና አእምሮአቸው ሳይጎዳ መማር እንዲችሉ ህክምና አግኝተው ከልጆች ጋር እንዲቀላቀሉ በሚያደርጉ ሁኔታዎች ዙሪያ ሰፋ ያለ ግንዛቤ እንደፈጠረላቸው ተናግረዋል።
በተጨማሪም በዲላ ዙሪያ ወረዳ አንዲዳ ጤና ጣቢያ ጎላ ጤና ኬላ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያ የሆኑት ወ/ሮ አስቴር ሽፈራው በበኩላቸው፤ እግራቸው ቆልመም ብሎ የሚወለዱትን ህፃናት እንዴት መታደግ እንደምንችል ህፃናት ከታከሙ እንደሚድኑ ግንዛቤ ማግኘታቸውን ገልፀዋል፡፡