Remedial
የተማሪዎች ጥሪ ማስታወቂያ
በሪሜዲያል ፕሮግራም ዲላ ዩኒቨርሲቲ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ
በ2016 ዓ.ም ዲላ ዩኒቨርሲቲ አዲስ የተመደባችሁ የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ወደ ዲላ ዩኒቨርሲቲ የምትገቡበትና የምትመዘገቡበት ቀን ጥር 23 እና 24/2016 ዓ.ም መሆኑን አውቃችሁ በተገለጸው ቀን ዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋናው ግቢ (ኦዳያኣ ካምፓስ) በሚገኘው ሬጂስትራር ጽ/ቤት በአካል ተገኝታችሁ እንድትመዘገቡ እናስታውቃለን፡፡
ለምዝገባ ስትመጡም፡-
1ኛ.የ8ተኛ ክፍል ካርድ ዋናውንና የማይመለስ አንድ ፎቶ ፒኮ፤
2ኛ. ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል የተማራችሁበትን ትራንስክሪፕት ዋናውንና የማይመለስ አንድ ፎቶ ኮፒ
3ኛ. 3×4 የሆነ የቅርብ ጊዜ ስምንት ጉርድ ፎቶ ግራፍ
4ኛ. አንሶላ፣ ብርድ ልብስና ትራስ ልብስ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ
ከተገለጸው ቀን ቀድሞም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የዲላ ዩኒቨርሲቲ ዋና ሬጂስትራር ጽ/ቤት

