ዲ.ዩ፤ ሐምሌ 11/2016ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የ2016 ዓ/ም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና ፈታኝ መምህራንና አስተባባሪዎች ሽኝት ተደረገላቸው።
ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት በሽኝት መርሐግብሩ ላይ ባደረጉት ንግግር፤ መንግሥት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅና አጠቃላይ የትምህርት ሪፎርምን ለማሳካት እያከናዎናቸው ካሉ ተግባራት አንዱ የሆነው የፈተና ኩረጃና ማጭበርበርን በማስቀረት ተማሪዎች በራሳቸው አቅም ለውጤት እንዲበቁ በማለም የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ መልቀቂያ ፈተና በዩኒቨርሲቲ ለ3ኛ ዙር መሰጠቱን አንስተው፤ ይህን አገራዊ ዓላማ ለማሳካት ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመምጣት ፈተናው በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ ርብርብ ላደረጉ የፈተና አስፈፃሚዎች በዩኒቨርሲቲው ስም ምስጋና አቅርበዋል።
ታምራት በየነ (ዶ/ር)፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት በበኩላቸው፤ የፈተና አስፈፃሚዎች ረጅም ርቀት ተጉዘው ከአየር መቀየር ጀምሮ የተለያዩ ተግዳሮቶችን ተቋቁመው ፈተናው በሰላምና በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ላበረከቱት አስተዋፅኦ ምስጋና በማቅረብ ወደየቤታቸው በሰላም እንዲገቡ ምኞታቸውን ገልጿል።
አስተያየት የሰጡን ፈታኝ መምህራን ዲላ ዩኒቨርሲቲ መልካም አቀባበል በማድረግ ፈተናው ሲጠናቀቅ እንዲህ አይነት የሽኝት መርሐግብር በማዘጋጀቱ ደስ መሰኘታቸውን ገልጸውልናል።
የሽኝቱ መርሃግብር ላይ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ባህል ማዕከል የሙዚቃ ስራዎችን በማቅረብ ፕሮግራሙን አድምቆታል።
ዲላ ዩኒቨርሲቲ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
ለወቅታዊ መረጃዎች
Facebook:
https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram: https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: pirdir@du.edu.et