በዩኒቨርሲቲው የተልዕኮ ልየታ ዙሪያ ከመምህራን ጋር ውይይት ተካሄደ፤
ዲ.ዩ፤ ጥር 22/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርስቲ መምህራን በተልዕኮ ልየታ (Differentiation) ስትራቴጂ ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።
ችሮታው አየለ (ዶ/ር)፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት አጠቃላይ የትምህርት ስረዓቱን ሪፎርም ለማድረግ ያስችል ዘንድ በተዘጋጀው የትምህርት ፍኖተ ካርታ የትምህርት ጥራት ከፍተኛ ትኩረት ተሰጥቶታል። በዚህም መሰረት የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ዩኒቨርሲቲዎችን በተልዕኮ መለየት በማስፈለጉ በትምህርት ሚኒስቴር የዩኒቨርሲቲዎች የተልዕኮ ልየታ ተሰርቷል
