Dilla University

Dilla University
ዲላ ዩኒቨርሲቲ

Green University, Sustainable Future

News
ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በይፋ ተጀመረ

ለ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች የሚሰጠው የማጠናከሪያ ትምህርት በይፋ ተጀመረ

ለአርሶ አደሮች የቡና ችግኝ ተሰራጨ

ለአርሶ አደሮች የቡና ችግኝ ተሰራጨ

Dilla University and ReWork Inc. Sign MOU to work in collaboration.

Dilla University and ReWork Inc. Sign MOU to work in collaboration.

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

ዲላ ዩኒቨርሲቲ “ስቴም” ማዕከል በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ልኡካን ተጎበኘ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

በቡሌ ወረዳ ለሚገኙ አርሶ አደሮች የምርጥ ዘር ድንች ስርጭት ተካሄደ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

“በገበያው ላይ ተወዳዳሪና በሙያቸው ተፈላጊ የሆኑ ምሩቃንን ለማፍራት መምህራን የማይተካ ሚና ይጫወታሉ!”ዶ/ር ታምራት በየነ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

በዛሬው እለትም የተሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ለአርሶ አደሮች ተሰራጩ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

ለመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ባለሙያዎች ተግባር ተኮር ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የመምህራንን የምርምር ተሳትፎ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ተሰጠ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

የተሻሻሉ የእንሰት ዝርያዎች ስርጭት ተካሄደ

Top News

ዲ.ዩ፤ ጥር 10/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርስቲ ማህበረሰብ አገልግሎት እና አጋርነት ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ለጌዴኦ ዞን፣ አባያና ዳራ ወረዳዎች የስፖርት ባለሙያዎች በእግር ኳስ አሰልጣኝነት እና ዳኝነት ሙያ ዙሪያ ለተከታታይ 5 ቀናት የቆየ ስልጠና መሰጠቱ ተገልጿል፡፡
በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት አቶ ብሩህ ተስፋሁን፣ የዲላ ዩኒቨርስቲ የማህበረሰብ አገልግሎት እና አጋርነት ዳይሬክቶሬት የስልጠናዎች አስተባባሪ እንደተናገሩት፤ ስልጠናው ቀስፖርቱ ዘርፍ ያሉ ባለሙያዎች በእግር ኳስ እውቀትና ክህሎት እንዲያዳብሩ፣ የተለያዩ ዓለም አቀፍ የስፖርት ህጎችን አውቀው የአሰልጣኝነትና የዳኝነት ልምዳቸውን እንዲያሳድጉ ያለመ መሆኑን ገልጸዋል።
ሰልጣኞች በአካባቢያቸው በየትምህርት ቤቶች ፕሮጀክቶችን በማቋቋም የወሰዱትን ስልጠና ወደ ተግባር እንዲቀይሩ ጭምር ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን አቶ ብሩህ አስገንዝበዋል።
ከአሰልጣኞች መካከል በዩኒቨርስቲው የስፖርት ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት መምህር ቸርነት ዳዊት እና መምህር አባያ ተፈራ እንደገለፁት፣ በእግርኳስ ስፖርት አሰልጣኝነትም ሆነ ዳኝነት በየጊዜው የሚደረጉ የህግ ለውጦችን ሰልጣኞች በአግባቡ እንዲያውቁና በየአካባቢው የሚደረጉ ጨዋታዎችን እንዲመሩ ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል፡፡
በስልጠናው መዝጊያ ንግግር ያደረጉት የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎትና አጋርነት ዳይሬክተር አቶ ተካልኝ ታደሰ በበኩላቸው፤ ስልጠናው የክህሎትና የእውቀት ክፍተት ለመሙላት የተሰጠ ስልጠና በመሆኑ ስልጠናውን የወሰዱ ሰልጣኞች ከስልጠናው ያገኙትን ክህሎት ወደ መሬት እንዲያወርዱና ተጨባጭ ስራ እንዲሰሩ አሳስበዋል።
ከስልጠናው ተሳታፊዎች መካከል የዲላ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ስፖርት መምህርት ምስጋና አንዳርጌ እና በይርጋጨፌ ወረዳ የዶማርሶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የስፖርት መምህር ሀብታሙ አለሙ እንደተናገሩት፤ ስልጠናው አዳዲስ የእግር ኳስ ህጎችና ቴክኒኮችን ያወቁበት፤ እንዲሁም በንድፈ ሃሳብ ያውቁት የነበረውን በተግባር ያዩበት እንደነበር ነግረውናል።
በስልጠናው ከጌዴኦ ዞን ስምንት ወረዳዎችና አምስት ከተማ አስተዳደሮች፣ ከሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳ እና ከምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ የተውጣጡ አጠቃላይ 30 ሰልጣኞች ተሳታፊ እንደነበሩ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ዲላ ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት

gtadmin