በቆልማማ እግር (Clubfoot) ልየታና የህክምና አገልግሎት ድጋፍ አሰጣጥ ዙሪያ ስልጠና ተሰጠ

ዲ.ዩ፤ የካቲት 02/2016 ዓ.ም. (ህ.ዓ.ግ)፦ “ሆፕ ወክስ” (HOPE WALKS) በጎ አድራጎት ድርጅት ከጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር በዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤና እና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል በመገኘት እግራቸው ቆልማማ በሆነ ታካሚዎች ዙሪያ ከጌዴኦ ዞን ዲላ ዙሪያ ወረዳ ለተወጣጡ 100 ለሚሆኑ የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ስልጠና የሰጠ ሲሆን በሆስፒታሉ ቆልማማ እግር ላላቸው ታካሚ ህፃናት የህክምና አገልግሎት ድጋፍ አድርጓል፡፡

Read more

ከቡና ልማት ምርታማነት ጋር ተያይዞ ያሉ ችግሮችን በምርምር መፍታት እንደሚገባ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ችሮታው አየለ ገለጹ፤

ዶ/ር ችሮታው አየለ ከኢትዮጵያ ቴሌቪዥን የልቦና ውቅር ፕሮግራም ጋር በነበራቸው ቆይታ ነው ከቡና ጋር የተያያዙ ችግሮችን በምርምር መፍታት እንደሚገባ የገለጹት።

Read more

የጌዴኦ ብሔር የቋንቋና ባህል ሲምፖዚየም ተካሄደ፤

ዲ.ዩ፤ የካቲት 1/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ እና የጌዴኦ ዞን አስተዳደር በትብብር ያዘጋጁት “ክብር ለአካባቢ ጥበቃ ጀግኖቻችን የጌዴኦ ማሕበረሰብ” በሚል መሪ ቃል የጌዴኦ ብሔር የቋንቋና ባህል- ዳራሮ ሲምፖዚየም ተካሂዷል።

Read more

በመውጫ ፈተና የላቀ አፈጻጸም ላስመዘገቡ ኮሌጆች እና ትምህርት ክፍሎች እውቅና እና ሽልማት ተሰጠ

ዲ.ዩ፤ ጥር 25/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ በ2015 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በተሰጠው የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ ኮሌጆች እና ትምህርት ክፍሎች እውቅና መሰጠቱ ተገልጿል።

Read more

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል በ2016 ዓ.ም በቅዳሜ እና እሁድ መርሐ ግብር የሚያስተምራቸውን አዲስ ተማሪዎች ተቀበለ፤

ዲ.ዩ፤ ጥር 26/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስቴም ማዕከል በ2016 ዓ.ም በቅዳሜ እና እሁድ መርሐ ግብር የሚያስተምራቸውን አዲስ ተማሪዎች ተቀብሎ የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሃ ግብር አካሂዷል።

Read more

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን በዛሬው እለት “አድዋ ለዘላቂ ሰላምና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ምክክር አካሂደዋል።

ታምራት በየነ (ዶ/ር)፤ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት እና የፕሬዝዳንቱ ተወካይ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ዓድዋ የሰው ልጅ ሰው መሆኑን ያረጋገጠበት፣ ጥቁር ከነጭ ጋር እኩል መሆኑን ያተመበት፤ አሸናፊ የሚኮነው በሚኖረው ጠንካራ ስብዕና እና በሚያዘው ፍትሃዊ ዓላማ እንጂ በመሳሪያ ጋጋታ እንዳልሆነ ያመላከተ ክስተት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

Read more

ዲላ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት እና ከጌዴኦ ማህበረሰብ ምስጋና ተቸረው፤

የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስትና ከጌዴኦ ማህበረሰብ ምስጋና የተቸረው የጌዴኦ ባህላዊ መልክዓምድር በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ድርጅት በአለም ቅርስ መዝገብ ላይ እንዲመዘገብ ላበረከተው ከፍተኛ አስተዋፅኦ ነው።

Read more