የተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ከመምህራን ውይይት አካሄዱ
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 12/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በመማር ማስተማር፣ በተልዕኮ ልየታ እና በዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ዙሪያ ከመምህራን ጋር ውይይት አካሂዷል።
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 12/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ በመማር ማስተማር፣ በተልዕኮ ልየታ እና በዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ዙሪያ ከመምህራን ጋር ውይይት አካሂዷል።
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 20/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ አጠቃላይ ሆስፒታል አዘጋጅነት በምርምር መረጃ አያያዝ እና አስተዳደር እንዲሁም በሰው ሰራሽ አስተውሎት ዙሪያ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቋል፡፡
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 19/2016 (ህ.ዓ.ግ)፦ 13ኛው አገር አቀፍ ዓመታዊ የምርምር ጉበኤ“ምርምር ለማህበረሰብ ለውጥ” በሚል ዋና ጭብጥ
በዲላ ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል። የዲላ ዩኒቨርሲቲ የምርምርና ቴክኖሎጂ ሽግግር ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት እና የምርምር፣ ህትመት፣ ሥነ ምግባርና ሥርፀት ዳይሬክቶሬት ጉባኤውን አሰናድተውታል።
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 17/2016 ዓ.ም፦ ዲላ ዩኒቨርሲቲ ወርልድ ቪዥን ኢትዮጵያ (WVE) በኮቾሬ ወረዳ ፍሥሃ-ገነት ከተማ ሲገለገልበት የቆየውን ሙሉ ግቢ ተረክቧል።
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 14/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ በሴቶች፣ ህፃናት እና ወጣቶች ጉዳይ ዳይሬክቶሬት አዘጋጅነት ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን “ሴቶችን እናብቃ፣ ልማትና ሰላምን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ሃሳብ ከዩኒቨርሲቲው አንጋፋ ሴት መምህራን ጋር የልምድ ልውውጥ በማድረግ በዓሉን በልዩ ልዩ ዝግጅቶች አክብሮ ውሏል። ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን በዓለም አቀፍ ደረጃ ለ113ኛ ጊዜ እንዲሁም በሀገራችን ደግሞ ለ48ኛ ጊዜ ተከብሮ መዋሉ ታውቋል።
ዲ.ዩ መጋቢት 11/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ በዲላ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅና አጠቃላይ ሆስፒታል አዘጋጅነት የምርምር ደረጃን የሚያሳይ የጥናትና ምርምር መረጃ አያያዝና አስተዳደር (Research Data management) እና በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አውድ በጤናው ዘርፍ ያሉ መርሆዎችን በተመለከተ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል፡፡
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 09/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አገልግሎት አጋርነት ዳይሬክቶሬት ከጌዴኦ ዞን፣ ከምዕራብ ጉጂ አባያ ወረዳ እና ከሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳ ለተወጣጡ የባህልና ቱሪዝም ባለሙያዎች በሀገር በቀል ዕውቀት ዙሪያ ሰልጠና ሰጥቷል፡፡
መጋቢት 05/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ም)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት አጋርነት ዳይሬክቶሬት በጌዴኦ ዞን ለሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች፣ በምዕራብ ጉጂ ዞን ለአባያ ወረዳ እና ለሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳ የንግድና ገበያ ልማት ባለሙያዎች በገበያ ጥናት መረጃ አሰባሰብ፣ ትንተናና ስርጭት ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱ ታውቋል።
ዲ.ዩ፤ መጋቢት 05/2016 ዓ/ም (ህ.ዓ.ግ)፦የዲላ ዩኒቨርሲቲ ኢንጂነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ 2ተኛውን ሳምንት የላብራቶሪ ኤግዚብሽን አካሂዷል።
አቶ ዮናስ ተጠምቀ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ አካዳሚክ ጉዳዮች ምክትል ፕሬዝዳንት ጽ/ቤት ኃላፊ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር እንደገለጹት፤ ላብራቶሪዎች ከፍተኛ በጀት ወጥቶባቸው የተገነቡ እንደመሆናቸው መጠን አጠቃላይ የኮሌጁ መምህራንና የላብራቶሪ አሲስታንቶች ላብራቶሪዎችን በሚገባ ተጠቅመው ከመማር ማስተማሩ ባለፈ ለተቋሙ የገቢ ምንጭነትም ጭምር እንዲሆኑ ማስቻል እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል።
ዲ.ዩ፤ የካቲት 04/2016 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ)፦ የዲላ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት አጋርነት ዳይሬክቶሬት ከጌዴኦ ዞን የተለያዩ ወረዳዎች፣ ከምዕራብ ጉጂ ዞን አባያ ወረዳ እና ከሲዳማ ክልል ዳራ ወረዳ ለተወጣጡ የማዘጋጃ ቤት እና የአካባቢ ጥበቃ ባለሙያዎች በተቀናጀ የደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ ዙሪያ ስልጠና ሰጥቷል፡፡