የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከል እና የህጻናት ማቆያ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል

ዲ.ዩ፤ መስከረም 26/2017 ዓ.ም (ህ.ዓ.ግ):- የዲላ ሆስፒታል ማስፋፊያ አካል የሆኑ የካንሰር ህክምና መስጫ ማዕከልን እና የህጻናት ማቆያ ማዕከልን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት እና የዲላ ዩኒቨርሲቲ ስራ አመራር ቦርድ አባል መርቀው ለአገልግሎት ክፍት አድርገዋል።
በአይነቱ የመጀመሪያ የሆነውና ዛሬ ተመሮቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው የካንሰር ህክምና ማዕከል ከፍተኛ ወጪ የሚጠይቀውን የካንሰር ህክምናን ለመፈለግ ወደሌላ ስፍራ ሲሄድ የነበረውን የአከባቢው ማህበረሰብ እንግልት የሚያስቀር ነው።
ሌላው በዛሬው እለት ተመርቆ ለአገልግሎት ክፍት የተደረገው የህጻናት ማቆያ ማዕከል፣ እድሜያቸው ከስድስት ወር እስከ ሶስት ዓመት የሆኑ ህጻናት ማቆያ ሲሆን ልጆቻቸውን የሚያጠቡ የሆስፒታሉ ሰራተኞች ተረጋግተው ውጤታማ ስራ እንዲሰሩ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
ማዕከላቱ የሆስፒታሉ ቦርድ ሰብሳቢ፣ የዲላ ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ አመራሮችና የሆስፒታሉ አመራሮች በተገኙበት ነው ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት የተደረጉት።
ዲላ፤
የአረንጓዴው ምድር ዩኒቨርሲቲ
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት
FB: https://www.facebook.com/Du.edu.et
Telegram:https://t.me/dprd9
website: https://www.du.edu.et
Email: https://www.pirdir@du.edu.et
